ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

external-link copy
91 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ ءَامِنُواْ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ نُؤۡمِنُ بِمَآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا وَيَكۡفُرُونَ بِمَا وَرَآءَهُۥ وَهُوَ ٱلۡحَقُّ مُصَدِّقٗا لِّمَا مَعَهُمۡۗ قُلۡ فَلِمَ تَقۡتُلُونَ أَنۢبِيَآءَ ٱللَّهِ مِن قَبۡلُ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

91. «አላህ ባወረደው እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው መጽሐፍ ብቻ እናምናለን» ይላሉ:: ከእርሱ ኋላ የመጣው ቁርኣን ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭና ትክክለኛ የሆነ ቢሆንም ይክዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነብያትን ለምን ገደላችሁ?» በላቸው። info
التفاسير: