ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

external-link copy
260 : 2

وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ رَبِّ أَرِنِي كَيۡفَ تُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰۖ قَالَ أَوَلَمۡ تُؤۡمِنۖ قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطۡمَئِنَّ قَلۡبِيۖ قَالَ فَخُذۡ أَرۡبَعَةٗ مِّنَ ٱلطَّيۡرِ فَصُرۡهُنَّ إِلَيۡكَ ثُمَّ ٱجۡعَلۡ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٖ مِّنۡهُنَّ جُزۡءٗا ثُمَّ ٱدۡعُهُنَّ يَأۡتِينَكَ سَعۡيٗاۚ وَٱعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

260. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ:: አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው:: ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ:: ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው:: አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው:: ከዚያ ቆራርጣቸው:: ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ:: ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ:: አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው:: info
التفاسير: