ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

external-link copy
246 : 2

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ مِنۢ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ مِنۢ بَعۡدِ مُوسَىٰٓ إِذۡ قَالُواْ لِنَبِيّٖ لَّهُمُ ٱبۡعَثۡ لَنَا مَلِكٗا نُّقَٰتِلۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۖ قَالَ هَلۡ عَسَيۡتُمۡ إِن كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡقِتَالُ أَلَّا تُقَٰتِلُواْۖ قَالُواْ وَمَا لَنَآ أَلَّا نُقَٰتِلَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَدۡ أُخۡرِجۡنَا مِن دِيَٰرِنَا وَأَبۡنَآئِنَاۖ فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقِتَالُ تَوَلَّوۡاْ إِلَّا قَلِيلٗا مِّنۡهُمۡۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ

246. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ ዘመን በኋላ ወደ ነበሩት የቤተ-ኢስራኢል ቅምጥሎች ተልኮላቸው ለነበረው ለነብያቸው «ለእኛ ንጉስን ሹምልን እና በአላህ መንገድ እንዋጋ።» ባሉ ጊዜ የሆነውን አላየህምን? እሱም «መዋጋት ቢፃፍባችሁ አትዋጉ ይሆናል።» አላቸው:: እነርሱም «ከአገሮቻችንና ከልጆቻችን ተባረን ሳለ በአላህ መንገድ የማንዋጋበት ምን ምክንያት አለን?» አሉ:: በእነርሱ ላይ መዋጋት በተፃፈባቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ ከመዋጋት አፈገፈጉ:: አላህ አጥፊዎችን ሁሉ በሚገባ ያውቃቸዋል:: info
التفاسير: