ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
80 : 16

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۢ بُيُوتِكُمۡ سَكَنٗا وَجَعَلَ لَكُم مِّن جُلُودِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ بُيُوتٗا تَسۡتَخِفُّونَهَا يَوۡمَ ظَعۡنِكُمۡ وَيَوۡمَ إِقَامَتِكُمۡ وَمِنۡ أَصۡوَافِهَا وَأَوۡبَارِهَا وَأَشۡعَارِهَآ أَثَٰثٗا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٖ

80. አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: ከእንስሳዎችም ቆዳዎችን በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 16

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّمَّا خَلَقَ ظِلَٰلٗا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡجِبَالِ أَكۡنَٰنٗا وَجَعَلَ لَكُمۡ سَرَٰبِيلَ تَقِيكُمُ ٱلۡحَرَّ وَسَرَٰبِيلَ تَقِيكُم بَأۡسَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ يُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُسۡلِمُونَ

81. አላህ ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን ፈጠረላችሁ:: ከጋራዎችም መከለያዎችን ፈጠረላችሁ:: ሐሩርንም ብርድንም የሚጠብቋችሁን ልብሶች፤ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ፈጠረላችሁ:: ልክ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 16

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ

82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስላም ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 16

يَعۡرِفُونَ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُنكِرُونَهَا وَأَكۡثَرُهُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ

83. የአላህን ጸጋ ያውቃሉ:: ሆኖም ከዚያ ይክዷታል:: አብዛኞቻቸዉም ከሓዲያን ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 16

وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدٗا ثُمَّ لَا يُؤۡذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُواْ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ

84. ከየህዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ:: ከዚያ ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 16

وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلۡعَذَابَ فَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ

85. እነዚያ የበደሉ ሰዎች ቅጣትን ባዩ ጊዜ ለእነርሱ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጣቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 16

وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ شُرَكَآءَهُمۡ قَالُواْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ شُرَكَآؤُنَا ٱلَّذِينَ كُنَّا نَدۡعُواْ مِن دُونِكَۖ فَأَلۡقَوۡاْ إِلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلَ إِنَّكُمۡ لَكَٰذِبُونَ

86. እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች ተጋሪዎቻቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ካንተ ሌላ እናመልካቸው የነበሩ ተጋሪዎቻችን ናቸው።» ይላሉ። አማልክቶችም «ውሸታሞች ናችሁ።» በማለት ቃሉን ወደ እነርሱው መልሰው ይወረውራሉ። info
التفاسير:

external-link copy
87 : 16

وَأَلۡقَوۡاْ إِلَى ٱللَّهِ يَوۡمَئِذٍ ٱلسَّلَمَۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

87. አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል:: info
التفاسير: