ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
19 : 13

۞ أَفَمَن يَعۡلَمُ أَنَّمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ ٱلۡحَقُّ كَمَنۡ هُوَ أَعۡمَىٰٓۚ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ

19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው ልክ እንደዚያ እርሱ እውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 13

ٱلَّذِينَ يُوفُونَ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ وَلَا يَنقُضُونَ ٱلۡمِيثَٰقَ

20. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 13

وَٱلَّذِينَ يَصِلُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ وَيَخَافُونَ سُوٓءَ ٱلۡحِسَابِ

21. እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፤ ጌታቸውንም የሚያከብሩ፤ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 13

وَٱلَّذِينَ صَبَرُواْ ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ رَبِّهِمۡ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ وَيَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عُقۡبَى ٱلدَّارِ

22. እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ ሰዎች እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው:: እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለችላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 13

جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنۡ ءَابَآئِهِمۡ وَأَزۡوَٰجِهِمۡ وَذُرِّيَّٰتِهِمۡۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَدۡخُلُونَ عَلَيۡهِم مِّن كُلِّ بَابٖ

23. እርሷም የመኖሪያ ገነቶች ናት:: ይገቡባታል:: ከአባቶቻቸዉም ከሚስቶቻቸዉም ከዝርያቸዉም መልካም የሠራ ሰው ሁሉ ይገባባታል። መላዕክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 13

سَلَٰمٌ عَلَيۡكُم بِمَا صَبَرۡتُمۡۚ فَنِعۡمَ عُقۡبَى ٱلدَّارِ

24. «ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ የተሰጣችሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 13

وَٱلَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهۡدَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مِيثَٰقِهِۦ وَيَقۡطَعُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱللَّعۡنَةُ وَلَهُمۡ سُوٓءُ ٱلدَّارِ

25. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ፤ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለእነርሱ እርግማን አለባቸው:: ለእነርሱም መጥፎ ሀገር ገሀነም አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 13

ٱللَّهُ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ وَفَرِحُواْ بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا مَتَٰعٞ

26. አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል:: ለሚሻውም ያጠባል:: ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ:: የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 13

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِيٓ إِلَيۡهِ مَنۡ أَنَابَ

27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደልትም?» ይላሉ:: «አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የተመለሰንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 13

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَطۡمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكۡرِ ٱللَّهِۗ أَلَا بِذِكۡرِ ٱللَّهِ تَطۡمَئِنُّ ٱلۡقُلُوبُ

28. እነርሱም እነዚያ በአላህ ያመኑ ልቦቻቸዉም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው:: አስተውሉ:: አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ:: info
التفاسير: