ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

external-link copy
41 : 8

۞ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا غَنِمۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا يَوۡمَ ٱلۡفُرۡقَانِ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

ከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የማረካችሁትን አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን ዕወቁ)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير: