ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

አል ሙዘሚል

external-link copy
1 : 73

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُزَّمِّلُ

አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 73

قُمِ ٱلَّيۡلَ إِلَّا قَلِيلٗا

ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 73

نِّصۡفَهُۥٓ أَوِ ٱنقُصۡ مِنۡهُ قَلِيلًا

ግማሹን (ቁም)፤ ወይም ከርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 73

أَوۡ زِدۡ عَلَيۡهِ وَرَتِّلِ ٱلۡقُرۡءَانَ تَرۡتِيلًا

ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 73

إِنَّا سَنُلۡقِي عَلَيۡكَ قَوۡلٗا ثَقِيلًا

እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 73

إِنَّ نَاشِئَةَ ٱلَّيۡلِ هِيَ أَشَدُّ وَطۡـٔٗا وَأَقۡوَمُ قِيلًا

የሌሊት መነሳት እርሷ (ሕዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 73

إِنَّ لَكَ فِي ٱلنَّهَارِ سَبۡحٗا طَوِيلٗا

ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም መዘዋወር አልለህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 73

وَٱذۡكُرِ ٱسۡمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلۡ إِلَيۡهِ تَبۡتِيلٗا

የጌታህንም ስም አውሳ፤ ወደእርሱም (መግገዛት) መቋረጥን ተቋረጥ ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 73

رَّبُّ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱتَّخِذۡهُ وَكِيلٗا

(እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 73

وَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱهۡجُرۡهُمۡ هَجۡرٗا جَمِيلٗا

(ከሓዲዎች) በሚሉትም ላይ ታገሥ፡፡ መልካምንም መተው ተዋቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 73

وَذَرۡنِي وَٱلۡمُكَذِّبِينَ أُوْلِي ٱلنَّعۡمَةِ وَمَهِّلۡهُمۡ قَلِيلًا

የድሎት ባለቤቶችም ከኾኑት አስተባባዮች ጋር ተዎኝ፡፡ ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 73

إِنَّ لَدَيۡنَآ أَنكَالٗا وَجَحِيمٗا

እኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎች እሳትም አልለና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 73

وَطَعَامٗا ذَا غُصَّةٖ وَعَذَابًا أَلِيمٗا

የሚያንቅ ምግብም፤ አሳማሚ ቅጣትም (አልለ) info
التفاسير:

external-link copy
14 : 73

يَوۡمَ تَرۡجُفُ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ وَكَانَتِ ٱلۡجِبَالُ كَثِيبٗا مَّهِيلًا

ምድርና ገራዎች በሚርገፈገፉበት፣ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚኾኑበት ቀን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 73

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ رَسُولٗا شَٰهِدًا عَلَيۡكُمۡ كَمَآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ رَسُولٗا

እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን ወደእናንተ ላክን፡፡ ወደ ፈርዖን መልክተኛን እንደላክን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 73

فَعَصَىٰ فِرۡعَوۡنُ ٱلرَّسُولَ فَأَخَذۡنَٰهُ أَخۡذٗا وَبِيلٗا

ፈርዖንም መልክተኛውን አመጸ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 73

فَكَيۡفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرۡتُمۡ يَوۡمٗا يَجۡعَلُ ٱلۡوِلۡدَٰنَ شِيبًا

ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 73

ٱلسَّمَآءُ مُنفَطِرُۢ بِهِۦۚ كَانَ وَعۡدُهُۥ مَفۡعُولًا

ሰማዩ በርሱ (በዚያ ቀን) ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 73

إِنَّ هَٰذِهِۦ تَذۡكِرَةٞۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلًا

ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ (መዳንን) የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ info
التفاسير: