ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

አስ ሶፍ

external-link copy
1 : 61

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሠ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 61

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفۡعَلُونَ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
3 : 61

كَبُرَ مَقۡتًا عِندَ ٱللَّهِ أَن تَقُولُواْ مَا لَا تَفۡعَلُونَ

የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 61

إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلَّذِينَ يُقَٰتِلُونَ فِي سَبِيلِهِۦ صَفّٗا كَأَنَّهُم بُنۡيَٰنٞ مَّرۡصُوصٞ

አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 61

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ لِمَ تُؤۡذُونَنِي وَقَد تَّعۡلَمُونَ أَنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡۖ فَلَمَّا زَاغُوٓاْ أَزَاغَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمۡۚ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

ሙሳም ለሕዝቦቹ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደእናንተ የአላህ መልክተኛ መኾኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡ ከእውነት) በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ info
التفاسير: