ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
32 : 42

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلۡجَوَارِ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ

በባሕር ላይ እንደ ጋራዎች ኾነው ተንሻላዮቹም (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 42

إِن يَشَأۡ يُسۡكِنِ ٱلرِّيحَ فَيَظۡلَلۡنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٍ

ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አልሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 42

أَوۡ يُوبِقۡهُنَّ بِمَا كَسَبُواْ وَيَعۡفُ عَن كَثِيرٖ

ወይም በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፡፡ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 42

وَيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ

(ከእነርሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፡፡ ለእነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 42

فَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَيۡءٖ فَمَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ

ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለእነዚያ ለአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 42

وَٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُواْ هُمۡ يَغۡفِرُونَ

ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት ለኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 42

وَٱلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِرَبِّهِمۡ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَمۡرُهُمۡ شُورَىٰ بَيۡنَهُمۡ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ

ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 42

وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَابَهُمُ ٱلۡبَغۡيُ هُمۡ يَنتَصِرُونَ

ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነርሱ (በመሰሉ) የሚመልሱ ለኾኑት (በላጭና ኗሪ ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 42

وَجَزَٰٓؤُاْ سَيِّئَةٖ سَيِّئَةٞ مِّثۡلُهَاۖ فَمَنۡ عَفَا وَأَصۡلَحَ فَأَجۡرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 42

وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعۡدَ ظُلۡمِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَا عَلَيۡهِم مِّن سَبِيلٍ

ከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 42

إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَظۡلِمُونَ ٱلنَّاسَ وَيَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት፣ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 42

وَلَمَن صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ

የታገስና ምሕረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 42

وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن وَلِيّٖ مِّنۢ بَعۡدِهِۦۗ وَتَرَى ٱلظَّٰلِمِينَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَ يَقُولُونَ هَلۡ إِلَىٰ مَرَدّٖ مِّن سَبِيلٖ

አላህ የሚያጠመውም ሰው ከእርሱ በኋለ ለእርሱ ምንም ረዳት የለውም፡፡ በደለኞችንም ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ወደ መመለስ መንገድ አልለን? የሚሉ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ info
التفاسير: