ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
39 : 41

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنَّكَ تَرَى ٱلۡأَرۡضَ خَٰشِعَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡۚ إِنَّ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاهَا لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

አንተ ምድርን ደረቅ ኾና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፡፡ በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ (በቡቃያዎችዋ) ትላወሳለች፡፡ ትነፋለችም፡፡ ያ ሕያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንን ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እነርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 41

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا لَا يَخۡفَوۡنَ عَلَيۡنَآۗ أَفَمَن يُلۡقَىٰ فِي ٱلنَّارِ خَيۡرٌ أَم مَّن يَأۡتِيٓ ءَامِنٗا يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ٱعۡمَلُواْ مَا شِئۡتُمۡ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ

እነዚያ አንቀጾቻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም፡፡ በእሳት ውስጥ የሚጣለው ሰው ይበልጣልን? ወይስ በትንሣኤ ቀን ጸጥተኛ ኾኖ የሚመጣው ሰው? የሻችሁትን ሥሩ (ዋጋችሁን ታገኛላችሁ)፡፡ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 41

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلذِّكۡرِ لَمَّا جَآءَهُمۡۖ وَإِنَّهُۥ لَكِتَٰبٌ عَزِيزٞ

እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 41

لَّا يَأۡتِيهِ ٱلۡبَٰطِلُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَلَا مِنۡ خَلۡفِهِۦۖ تَنزِيلٞ مِّنۡ حَكِيمٍ حَمِيدٖ

ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 41

مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدۡ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبۡلِكَۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٖ

ካንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ብጤ እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፡፡ ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 41

وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَانًا أَعۡجَمِيّٗا لَّقَالُواْ لَوۡلَا فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥٓۖ ءَا۬عۡجَمِيّٞ وَعَرَبِيّٞۗ قُلۡ هُوَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ هُدٗى وَشِفَآءٞۚ وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٞ وَهُوَ عَلَيۡهِمۡ عَمًىۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُنَادَوۡنَ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ

በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ «(በምናውቀው ቋንቋ) አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አጀምኛና (መልክተኛው) ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡ እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው፡፡ (አይሰሙትም)፡፡ እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጥጠሩ ናቸው፡፡ {1} info

{1} አጀምኛ ማለት ከአረብኛ ውጪ ያሉ ቋንቋዎች ማለት ነው።

التفاسير:

external-link copy
45 : 41

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ

ሙሳንም መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በእርሱም ተለያዩበት፡፡ ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፡፡ እነርሱም ከእርሱ አወላዋይ በኾነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 41

مَّنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ

መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም፡፡ info
التفاسير: