ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
8 : 34

أَفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَم بِهِۦ جِنَّةُۢۗ بَلِ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ فِي ٱلۡعَذَابِ وَٱلضَّلَٰلِ ٱلۡبَعِيدِ

በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበትን? (አሉ)፡፡ እንዳሉት አይደለም፡፡ እነዚያ በመጨረሻይቱ (ዓለም) የሚያምኑት (በእርሷ) በቅጣት ውስጥ (አሁን) በራቀ ስህተትም ውስጥ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 34

أَفَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَىٰ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِن نَّشَأۡ نَخۡسِفۡ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضَ أَوۡ نُسۡقِطۡ عَلَيۡهِمۡ كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّكُلِّ عَبۡدٖ مُّنِيبٖ

ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወዳለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ በእነርሱ ምድርን እንደረባባቸዋለን፡፡ ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን፤ በዚህ ውስጥ (ወደ ጌታው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ምልክት አለበት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 34

۞ وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ مِنَّا فَضۡلٗاۖ يَٰجِبَالُ أَوِّبِي مَعَهُۥ وَٱلطَّيۡرَۖ وَأَلَنَّا لَهُ ٱلۡحَدِيدَ

ለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልንም)፡-«ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፡፡ በራሪዎችንም (ገራንለት)፡፡ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
11 : 34

أَنِ ٱعۡمَلۡ سَٰبِغَٰتٖ وَقَدِّرۡ فِي ٱلسَّرۡدِۖ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

ሰፋፊዎችን ጥሩሮች ሥራ፡፡ በአሠራርዋም መጥን፡፡ መልካምንም ሥራ ሥሩ፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 34

وَلِسُلَيۡمَٰنَ ٱلرِّيحَ غُدُوُّهَا شَهۡرٞ وَرَوَاحُهَا شَهۡرٞۖ وَأَسَلۡنَا لَهُۥ عَيۡنَ ٱلۡقِطۡرِۖ وَمِنَ ٱلۡجِنِّ مَن يَعۡمَلُ بَيۡنَ يَدَيۡهِ بِإِذۡنِ رَبِّهِۦۖ وَمَن يَزِغۡ مِنۡهُمۡ عَنۡ أَمۡرِنَا نُذِقۡهُ مِنۡ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ

ለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲኾን ገራንለት፡፡ የነሐስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት፡፡ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሠሩን (አደረግንለት)፡፡ ከነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 34

يَعۡمَلُونَ لَهُۥ مَا يَشَآءُ مِن مَّحَٰرِيبَ وَتَمَٰثِيلَ وَجِفَانٖ كَٱلۡجَوَابِ وَقُدُورٖ رَّاسِيَٰتٍۚ ٱعۡمَلُوٓاْ ءَالَ دَاوُۥدَ شُكۡرٗاۚ وَقَلِيلٞ مِّنۡ عِبَادِيَ ٱلشَّكُورُ

ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል፡፡ (አልናቸውም) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! አመስጋኞች ኾናችሁ (ለጌታችሁ) ሥሩ፡፡» ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 34

فَلَمَّا قَضَيۡنَا عَلَيۡهِ ٱلۡمَوۡتَ مَا دَلَّهُمۡ عَلَىٰ مَوۡتِهِۦٓ إِلَّا دَآبَّةُ ٱلۡأَرۡضِ تَأۡكُلُ مِنسَأَتَهُۥۖ فَلَمَّا خَرَّ تَبَيَّنَتِ ٱلۡجِنُّ أَن لَّوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ ٱلۡغَيۡبَ مَا لَبِثُواْ فِي ٱلۡعَذَابِ ٱلۡمُهِينِ

በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን በትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸውም፡፡ በወደቀ ጊዜም ጋኔኖች ሩቅን ምስጢር የሚያወቁ በኾኑ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆይ እንደነበሩ ተረዱ፡፡ info
التفاسير: