ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
7 : 33

وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِيثَٰقَهُمۡ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٖ وَإِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ٱبۡنِ مَرۡيَمَۖ وَأَخَذۡنَا مِنۡهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا

ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ (አስታወስ)፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 33

لِّيَسۡـَٔلَ ٱلصَّٰدِقِينَ عَن صِدۡقِهِمۡۚ وَأَعَدَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابًا أَلِيمٗا

(አላህ) እውነተኞችን ከውነታቸው ሊጠይቅ (ይህንን ሠራ)፡፡ ለከሓዲዎችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 33

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ جَآءَتۡكُمۡ جُنُودٞ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا وَجُنُودٗا لَّمۡ تَرَوۡهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣችባችሁና በእነርሱ ላይ ነፋስንና ያላያችኋትን ሰራዊት በላክን ጊዜ በእናንተ ላይ (ያደረገላችሁን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 33

إِذۡ جَآءُوكُم مِّن فَوۡقِكُمۡ وَمِنۡ أَسۡفَلَ مِنكُمۡ وَإِذۡ زَاغَتِ ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَبَلَغَتِ ٱلۡقُلُوبُ ٱلۡحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِٱللَّهِ ٱلظُّنُونَا۠

ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ ጊዜ፣ ዓይኖችም በቃበዙ፣ ልቦችም ላንቃዎች በደረሱና በአላህም ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ (ያደረገላችሁን አስታውሱ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 33

هُنَالِكَ ٱبۡتُلِيَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَزُلۡزِلُواْ زِلۡزَالٗا شَدِيدٗا

እዚያ ዘንድ ምእምናን ተሞከሩ፡፡ ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 33

وَإِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ مَّا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ إِلَّا غُرُورٗا

መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸውም «አላህና መልክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም» በሚሉ ጊዜ (ያደረገላችሁን አስታውሱ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 33

وَإِذۡ قَالَت طَّآئِفَةٞ مِّنۡهُمۡ يَٰٓأَهۡلَ يَثۡرِبَ لَا مُقَامَ لَكُمۡ فَٱرۡجِعُواْۚ وَيَسۡتَـٔۡذِنُ فَرِيقٞ مِّنۡهُمُ ٱلنَّبِيَّ يَقُولُونَ إِنَّ بُيُوتَنَا عَوۡرَةٞ وَمَا هِيَ بِعَوۡرَةٍۖ إِن يُرِيدُونَ إِلَّا فِرَارٗا

ከእነርሱም የሆኑ ጭፍሮች «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ» ባሉ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ከእነርሱም «ከፊሎቹ እርሷ ነውረኛ ሳትሆን ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው» የሚሉ ሆነው ነቢዩን (ከጦሩ ለመመለስ) ፈቃድን ይጠይቃሉ፡፡ መሸሽን እንጂ ሌላ አይፈልጉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 33

وَلَوۡ دُخِلَتۡ عَلَيۡهِم مِّنۡ أَقۡطَارِهَا ثُمَّ سُئِلُواْ ٱلۡفِتۡنَةَ لَأٓتَوۡهَا وَمَا تَلَبَّثُواْ بِهَآ إِلَّا يَسِيرٗا

በእነርሱም ላይ (ቤቶቻቸው) ከየቀበሌዋ በተገባባት ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በሠሯት ነበር፡፡ በእርሷም ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 33

وَلَقَدۡ كَانُواْ عَٰهَدُواْ ٱللَّهَ مِن قَبۡلُ لَا يُوَلُّونَ ٱلۡأَدۡبَٰرَۚ وَكَانَ عَهۡدُ ٱللَّهِ مَسۡـُٔولٗا

ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያ በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የተጋቡ ነበሩ፡፡ የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ነው፡፡ info
التفاسير: