ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
22 : 28

وَلَمَّا تَوَجَّهَ تِلۡقَآءَ مَدۡيَنَ قَالَ عَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يَهۡدِيَنِي سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ

ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም «ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 28

وَلَمَّا وَرَدَ مَآءَ مَدۡيَنَ وَجَدَ عَلَيۡهِ أُمَّةٗ مِّنَ ٱلنَّاسِ يَسۡقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ ٱمۡرَأَتَيۡنِ تَذُودَانِۖ قَالَ مَا خَطۡبُكُمَاۖ قَالَتَا لَا نَسۡقِي حَتَّىٰ يُصۡدِرَ ٱلرِّعَآءُۖ وَأَبُونَا شَيۡخٞ كَبِيرٞ

ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ በእርሱ ላይ ከሰዎች ጭፍሮችን (መንጋዎቻቸውን) የሚያጠጡ ሆነው አገኘ፡፡ ከእነርሱ በታችም (ከውሃው መንጎቻቸውን) የሚከለክሉን ሁለት ሴቶች አገኘ፡፡ «ነገራችሁ ምንድን ነው؟» አላቸው፡፡ «እረኞቹ ሁሉ (መንጋዎቻቸውን) እስከሚመልሱ አናጠጣም፡፡ አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 28

فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰٓ إِلَى ٱلظِّلِّ فَقَالَ رَبِّ إِنِّي لِمَآ أَنزَلۡتَ إِلَيَّ مِنۡ خَيۡرٖ فَقِيرٞ

ለሁለቱም አጠጣላቸው፡፡ ከዚያም ወደ ጥላው ዘወር አለ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 28

فَجَآءَتۡهُ إِحۡدَىٰهُمَا تَمۡشِي عَلَى ٱسۡتِحۡيَآءٖ قَالَتۡ إِنَّ أَبِي يَدۡعُوكَ لِيَجۡزِيَكَ أَجۡرَ مَا سَقَيۡتَ لَنَاۚ فَلَمَّا جَآءَهُۥ وَقَصَّ عَلَيۡهِ ٱلۡقَصَصَ قَالَ لَا تَخَفۡۖ نَجَوۡتَ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትኼድ ሆና መጣችው፡፡ «አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል» አለችው፡፡ ወደእርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ «አትፍራ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ድነሃል» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 28

قَالَتۡ إِحۡدَىٰهُمَا يَٰٓأَبَتِ ٱسۡتَـٔۡجِرۡهُۖ إِنَّ خَيۡرَ مَنِ ٱسۡتَـٔۡجَرۡتَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡأَمِينُ

ከሁለቱ አንደኛይቱም «አባቴ ሆይ ቅጠረው፡፡ ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ ብርቱው ታማኙ ነውና» አለችው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 28

قَالَ إِنِّيٓ أُرِيدُ أَنۡ أُنكِحَكَ إِحۡدَى ٱبۡنَتَيَّ هَٰتَيۡنِ عَلَىٰٓ أَن تَأۡجُرَنِي ثَمَٰنِيَ حِجَجٖۖ فَإِنۡ أَتۡمَمۡتَ عَشۡرٗا فَمِنۡ عِندِكَۖ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أَشُقَّ عَلَيۡكَۚ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

«ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶቸ ልጆቼ አንዲቱን ላጋባህ እሻለሁ፡፡ ዐስርን ብትሞላም ከአንተ ነው፡፡ ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም፡፡ አላህ የሻ እንደ ኾነ ከመልካሞቹ ሰዎች ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 28

قَالَ ذَٰلِكَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَۖ أَيَّمَا ٱلۡأَجَلَيۡنِ قَضَيۡتُ فَلَا عُدۡوَٰنَ عَلَيَّۖ وَٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٞ

(ሙሳም) «ይህ (ውለታ) በእኔና ባንተ መካከል (ረጊ) ነው፡፡ ከሁለቱ ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም፡፡ አላህም በምንለው ላይ ምስክር» ነው አለ፡፡ info
التفاسير: