ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
23 : 27

إِنِّي وَجَدتُّ ٱمۡرَأَةٗ تَمۡلِكُهُمۡ وَأُوتِيَتۡ مِن كُلِّ شَيۡءٖ وَلَهَا عَرۡشٌ عَظِيمٞ

«እኔ የምትገዛቸው የኾኑችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችኝ አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 27

وَجَدتُّهَا وَقَوۡمَهَا يَسۡجُدُونَ لِلشَّمۡسِ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَصَدَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ فَهُمۡ لَا يَهۡتَدُونَ

«እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
25 : 27

أَلَّاۤ يَسۡجُدُواْۤ لِلَّهِ ٱلَّذِي يُخۡرِجُ ٱلۡخَبۡءَ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَيَعۡلَمُ مَا تُخۡفُونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ

ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገ ልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 27

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ۩

አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው፡፡ {1} info

{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱትላዋ) ይደረጋል።

التفاسير:

external-link copy
27 : 27

۞ قَالَ سَنَنظُرُ أَصَدَقۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

(ሱለይማንም) አለ «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ኾንክ ወደፊት እናያለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 27

ٱذۡهَب بِّكِتَٰبِي هَٰذَا فَأَلۡقِهۡ إِلَيۡهِمۡ ثُمَّ تَوَلَّ عَنۡهُمۡ فَٱنظُرۡ مَاذَا يَرۡجِعُونَ

«ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ኺድ፡፡ ወደእነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ ምን አንደሚመልሱም ተመልከት፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
29 : 27

قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ إِنِّيٓ أُلۡقِيَ إِلَيَّ كِتَٰبٞ كَرِيمٌ

(እርሷም በደረሳት ጊዜ) አለች «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደኔ ተጣለ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 27

إِنَّهُۥ مِن سُلَيۡمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

«እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 27

أَلَّا تَعۡلُواْ عَلَيَّ وَأۡتُونِي مُسۡلِمِينَ

«በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ፤ (የሚል ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 27

قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ أَفۡتُونِي فِيٓ أَمۡرِي مَا كُنتُ قَاطِعَةً أَمۡرًا حَتَّىٰ تَشۡهَدُونِ

«እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ (የሚበጀውን) ንገሩኝ፡፡ እስከምትገኙልኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 27

قَالُواْ نَحۡنُ أُوْلُواْ قُوَّةٖ وَأُوْلُواْ بَأۡسٖ شَدِيدٖ وَٱلۡأَمۡرُ إِلَيۡكِ فَٱنظُرِي مَاذَا تَأۡمُرِينَ

«እኛ የኀይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን፡፡ ግን ትዕዛዙ ወደ አንቺ ነው፡፡ ምን እንደምታዢም አስተውዪ፤» አሏት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 27

قَالَتۡ إِنَّ ٱلۡمُلُوكَ إِذَا دَخَلُواْ قَرۡيَةً أَفۡسَدُوهَا وَجَعَلُوٓاْ أَعِزَّةَ أَهۡلِهَآ أَذِلَّةٗۚ وَكَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ

(እርሷም) አለች «ንጉሦች ከተማን (በኀይል) በገቡባት ጊዜ ያበላሹዋታል፡፡ የተከበሩ ሰዎችዋንም ወራዶች ያደርጋሉ፡፡ እንደዚሁም (እነዚህ) ይሠራሉ፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 27

وَإِنِّي مُرۡسِلَةٌ إِلَيۡهِم بِهَدِيَّةٖ فَنَاظِرَةُۢ بِمَ يَرۡجِعُ ٱلۡمُرۡسَلُونَ

«እኔም ወደእነርሱ ገጸ በረከትን የምልክና መልክተኞቹ በምን እንደሚመለሱ የምጠባበቅ ነኝ፡፡» info
التفاسير: