Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

አል ዐለቅ

external-link copy
1 : 96

ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! {1} info

{1} ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ከቁርአን መጀመሪያ የወረዱ አንቀጾች ናቸው። በኑር ተራራ ላይ በምገኘው የሂራእ ዋሻ ውስጥ ነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ኸልዋ ወጥተው እያሉ ነው የወረደባቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም፤ የወህይ አጀማመር ምእራፍ)

التفاسير:

external-link copy
2 : 96

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ

2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም):: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 96

ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 96

ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ

4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 96

عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ

5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ):: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 96

كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ

6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 96

أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ

7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት info
التفاسير:

external-link copy
8 : 96

إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ

8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 96

أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ

9. ያንን የሚከለክለውን አየህን? info
التفاسير:

external-link copy
10 : 96

عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ

10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን): info
التفاسير:

external-link copy
11 : 96

أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ

11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 96

أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ

12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 96

أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ

13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 96

أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ

14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን? info
التفاسير:

external-link copy
15 : 96

كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ

15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ አናቱን ይዘን አንጎትተዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 96

نَاصِيَةٖ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٖ

16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 96

فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ

17. ሸንጎውንም ይጥራ፤ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 96

سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ

18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 96

كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩

19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። {1} info

{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ አለ። ይህ የመጨረሻ ሱጁድ ነው።

التفاسير: