Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

አል ኢንሳን

external-link copy
1 : 76

هَلۡ أَتَىٰ عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ حِينٞ مِّنَ ٱلدَّهۡرِ لَمۡ يَكُن شَيۡـٔٗا مَّذۡكُورًا

1. በሰው ላይ የሚታወስ ነገር (እንኳ) ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ አላለፈም ነበርን? (በእርግጥ አልፏል)። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 76

إِنَّا خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن نُّطۡفَةٍ أَمۡشَاجٖ نَّبۡتَلِيهِ فَجَعَلۡنَٰهُ سَمِيعَۢا بَصِيرًا

2. እኛ ሰውን (በሕግጋት ግዳጅ) የምንሞክረው ስንሆን ከወንድና ከሴት ፈሳሽ ቅልቅሎች ከሆነች የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው:: ሰሚና ተመልካችም አደረግነው። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 76

إِنَّا هَدَيۡنَٰهُ ٱلسَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرٗا وَإِمَّا كَفُورًا

3. እኛ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲሆን መንገዱን መራነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 76

إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ سَلَٰسِلَاْ وَأَغۡلَٰلٗا وَسَعِيرًا

4. እኛ ለከሓዲያን ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም (አዘጋጅተናል):: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 76

إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ يَشۡرَبُونَ مِن كَأۡسٖ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا

5. እነዚያ (ትክክለኛ) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 76

عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا عِبَادُ ٱللَّهِ يُفَجِّرُونَهَا تَفۡجِيرٗا

6. ከእርሷ እነዚያ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት ና ወደ ፈለጉበት ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከሆነች የጠጅ ምንጭ (ይጠጣሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 76

يُوفُونَ بِٱلنَّذۡرِ وَيَخَافُونَ يَوۡمٗا كَانَ شَرُّهُۥ مُسۡتَطِيرٗا

7. (ዛሬ በዚህ ዓለም እያሉ) በስለታቸው ይሞላሉ:: መከራው ተሰራጪ የሆነንም ቀን ይፈራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 76

وَيُطۡعِمُونَ ٱلطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ مِسۡكِينٗا وَيَتِيمٗا وَأَسِيرًا

8. ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፤ ለየቲምና ለምርኮኛ ያበላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 76

إِنَّمَا نُطۡعِمُكُمۡ لِوَجۡهِ ٱللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمۡ جَزَآءٗ وَلَا شُكُورًا

9. «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው:: ከናንተ ክፍያንም ሆነ ማመስገንን አንፈልግም:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 76

إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوۡمًا عَبُوسٗا قَمۡطَرِيرٗا

10. እኛ ያንን (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» (ይላሉ)። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 76

فَوَقَىٰهُمُ ٱللَّهُ شَرَّ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمِ وَلَقَّىٰهُمۡ نَضۡرَةٗ وَسُرُورٗا

11. አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው። (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 76

وَجَزَىٰهُم بِمَا صَبَرُواْ جَنَّةٗ وَحَرِيرٗا

12. በመታገሳቸዉም (ምክንያት) ገነትንና የሀር ልብስን መነዳቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 76

مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِۖ لَا يَرَوۡنَ فِيهَا شَمۡسٗا وَلَا زَمۡهَرِيرٗا

13. በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች፤ በውስጧ የጸሀይን ሐሩርንም ሆነ ብርድንም የማያዩ ሲሆኑ፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 76

وَدَانِيَةً عَلَيۡهِمۡ ظِلَٰلُهَا وَذُلِّلَتۡ قُطُوفُهَا تَذۡلِيلٗا

14. ዛፎቿም ለእነርሱ የቀረበች፤ ፍራፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መገራትን የተገራች ስትሆን ገነትን መነዳቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 76

وَيُطَافُ عَلَيۡهِم بِـَٔانِيَةٖ مِّن فِضَّةٖ وَأَكۡوَابٖ كَانَتۡ قَوَارِيرَا۠

15. በእነርሱም ላይ ከብር በተሰሩ ዕቃዎች (ሳህኖች)፤ ብርጭቆዎች እና በኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 76

قَوَارِيرَاْ مِن فِضَّةٖ قَدَّرُوهَا تَقۡدِيرٗا

16. መለካትን የለኳቸው በሆኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል):: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 76

وَيُسۡقَوۡنَ فِيهَا كَأۡسٗا كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلًا

17. በእርሷም መበረዣዋ ዝንጂብል የሆነች ወይን ጠጅ ይጥጠጣሉ። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 76

عَيۡنٗا فِيهَا تُسَمَّىٰ سَلۡسَبِيلٗا

18. በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 76

۞ وَيَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ وِلۡدَٰنٞ مُّخَلَّدُونَ إِذَا رَأَيۡتَهُمۡ حَسِبۡتَهُمۡ لُؤۡلُؤٗا مَّنثُورٗا

19. በእነርሱም ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ:: ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 76

وَإِذَا رَأَيۡتَ ثَمَّ رَأَيۡتَ نَعِيمٗا وَمُلۡكٗا كَبِيرًا

20. እዚያንም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግስናን ታያለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 76

عَٰلِيَهُمۡ ثِيَابُ سُندُسٍ خُضۡرٞ وَإِسۡتَبۡرَقٞۖ وَحُلُّوٓاْ أَسَاوِرَ مِن فِضَّةٖ وَسَقَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡ شَرَابٗا طَهُورًا

21. አረንጓዴዎች የሆኑ ቀጭን ሀር ልብሶችና ወፍራም ሀርም በላያቸው ላይ አለ። ከብር የሆኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ:: ጌታቸዉም (ከራሱ አልፎ) ሌላን አጥሪ የሆነን መጠጥ ያጠጣቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 76

إِنَّ هَٰذَا كَانَ لَكُمۡ جَزَآءٗ وَكَانَ سَعۡيُكُم مَّشۡكُورًا

22. «ይህ ለእናንተ ዋጋ ሆነ:: ስራችሁም ምስጉን ሆነ» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 76

إِنَّا نَحۡنُ نَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ تَنزِيلٗا

23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ (ይህንን) ቁርኣን ባንተ ላይ ማውረድን አወረድነው። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 76

فَٱصۡبِرۡ لِحُكۡمِ رَبِّكَ وَلَا تُطِعۡ مِنۡهُمۡ ءَاثِمًا أَوۡ كَفُورٗا

24. ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: ከእነርሱም መካከል ኃጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 76

وَٱذۡكُرِ ٱسۡمَ رَبِّكَ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلٗا

25. የጌታህን ስም በጠዋትና ከቀትር በኋላ አውሳ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 76

وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَٱسۡجُدۡ لَهُۥ وَسَبِّحۡهُ لَيۡلٗا طَوِيلًا

26 ከሌሊቱም ለእርሱ ብቻ ስገድ፤ በረዢም ሌሊትም አወድሰው። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 76

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ يُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ وَيَذَرُونَ وَرَآءَهُمۡ يَوۡمٗا ثَقِيلٗا

27. እነዚያ ይህችን ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ። ከባድና (አስቸጋሪ) ቀንም በስተፊታቸው ሆኖ ችላ ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 76

نَّحۡنُ خَلَقۡنَٰهُمۡ وَشَدَدۡنَآ أَسۡرَهُمۡۖ وَإِذَا شِئۡنَا بَدَّلۡنَآ أَمۡثَٰلَهُمۡ تَبۡدِيلًا

28. እኛ ፈጠርናቸው:: የአካሎቻቸዉንም መለያያቸውን አጠነከርን:: በፈለግን ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 76

إِنَّ هَٰذِهِۦ تَذۡكِرَةٞۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلٗا

29. ይህ መገሰጫ ነው:: የፈለገ ሰውም ወደ ጌታው መንገድ ይይዛል:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 76

وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمٗا

30. አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፤ አላህ አዋቂና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 76

يُدۡخِلُ مَن يَشَآءُ فِي رَحۡمَتِهِۦۚ وَٱلظَّٰلِمِينَ أَعَدَّ لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمَۢا

31. (አላህ) የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዩችንም (ዝቶባቸዋል) ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል:: info
التفاسير: