Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

አል መዓሪጅ

external-link copy
1 : 70

سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابٖ وَاقِعٖ

1. ወዳቂ (ተከሳች) ከሆነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 70

لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعٞ

2. ከሓዲያን ላይ (ወዳቂ ከሆነው) ለእርሱ መላሽ የለዉም። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 70

مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ

3. የ (ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም):: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 70

تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةٖ

4. መላዕክትና መንፈሱም ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ (ይወጣሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 70

فَٱصۡبِرۡ صَبۡرٗا جَمِيلًا

5. መልካምን ትዕግስት ታገስ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 70

إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدٗا

6. እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 70

وَنَرَىٰهُ قَرِيبٗا

7. እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 70

يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ

8. ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 70

وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ

9. ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ንፋስ) እንደበተነውና እንደሚያበረው በሚሆኑበት ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 70

وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمٗا

10. ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን መላሽ የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 70

يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ

11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 70

وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ

12. በሚስቱም በወንድሙም፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 70

وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ

13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 70

وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ

14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል):: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 70

كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ

15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 70

نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ

16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 70

تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ

17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 70

وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ

18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች):: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 70

۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا

19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 70

إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا

20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 70

وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا

21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 70

إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ

22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 70

ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ

23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 70

وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ

24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 70

لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ

25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 70

وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 70

وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ

27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 70

إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ

28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ

29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 70

إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ

30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 70

فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ

31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ

32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 70

وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ

33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ

34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 70

أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ

35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 70

فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ

36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 70

عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ

37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 70

أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ

38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? info
التفاسير:

external-link copy
39 : 70

كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ

39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 70

فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 70

عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ

41. ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 70

فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ

42. ያንንም የሚሰፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 70

يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعٗا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبٖ يُوفِضُونَ

43. ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 70

خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ

44. ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች:: ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው:: info
التفاسير: