Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

አል ፈትህ

external-link copy
1 : 48

إِنَّا فَتَحۡنَا لَكَ فَتۡحٗا مُّبِينٗا

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ (መካን) በመክፈት ግልጽ የሆነን ድል ለገስንህ። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 48

لِّيَغۡفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَيَهۡدِيَكَ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا

2. አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትክን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 48

وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصۡرًا عَزِيزًا

3. አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ መካን ከፈተልህ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 48

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لِيَزۡدَادُوٓاْ إِيمَٰنٗا مَّعَ إِيمَٰنِهِمۡۗ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

4. አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው:: አላህ የሰማይና የምድር ስራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 48

لِّيُدۡخِلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوۡزًا عَظِيمٗا

5. ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (መካን ከፈተልህ):: ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 48

وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِۚ عَلَيۡهِمۡ دَآئِرَةُ ٱلسَّوۡءِۖ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَلَعَنَهُمۡ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرٗا

6. በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ወንድ ተጣራጣሪ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን ወንድ አጋሪዎችና ሴት አጋሪዎችን ያሰቃይም ዘንድ (በትግል አዘዘ):: በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው:: በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም:: ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው:: ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 48

وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

7. ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 48

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 48

لِّتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُۚ وَتُسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا

9. በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)። info
التفاسير: