Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

Nomor Halaman:close

external-link copy
60 : 28

وَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَيۡءٖ فَمَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتُهَاۚ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

60. ሰዎች ሆይ! በማንኛዉም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሂይወት ጥቅምና ጌጣ ጌጥ ነው:: አላህ ዘንድ ያለዉም ምንዳ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው:: አታውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
61 : 28

أَفَمَن وَعَدۡنَٰهُ وَعۡدًا حَسَنٗا فَهُوَ لَٰقِيهِ كَمَن مَّتَّعۡنَٰهُ مَتَٰعَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا ثُمَّ هُوَ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ

61. መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያ እርሱ በትንሳኤ ቀን ለእሳት ከሚቀረቡት እንደ ሆነው ሰው ነውን? info
التفاسير:

external-link copy
62 : 28

وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ

62. (አላህ) የሚጠራባቸውንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን (አስታውስ):: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 28

قَالَ ٱلَّذِينَ حَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلُ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَغۡوَيۡنَآ أَغۡوَيۡنَٰهُمۡ كَمَا غَوَيۡنَاۖ تَبَرَّأۡنَآ إِلَيۡكَۖ مَا كَانُوٓاْ إِيَّانَا يَعۡبُدُونَ

63. እነዚያ በእነርሱ ላይ ቅጣቱ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፤ እንደጠመምን አጠመምናቸው (ከእነርሱ) ወደ አንተ ተጥራራን:: እኛን ይገዙ አልነበሩም።» info
التفاسير:

external-link copy
64 : 28

وَقِيلَ ٱدۡعُواْ شُرَكَآءَكُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَرَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۚ لَوۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ يَهۡتَدُونَ

64. «ለአላህ የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ:: ይጠሩዋቸዋልም ግን ለእነርሱ አይመልሱላቸዉም:: ቅጣትንም ያያሉ፤ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር):: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 28

وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ مَاذَآ أَجَبۡتُمُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

65. የሚጠራባቸውንና «ለመልዕክተኞች ምንን መለሳችሁ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 28

فَعَمِيَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَنۢبَآءُ يَوۡمَئِذٖ فَهُمۡ لَا يَتَسَآءَلُونَ

66. በዚያም ቀን ወሬዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰወሩባቸዋል፤ እነርሱም አይጠያየቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 28

فَأَمَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَعَسَىٰٓ أَن يَكُونَ مِنَ ٱلۡمُفۡلِحِينَ

67. የተጸጸተና ያመነማ መልካምንም የሰራ ከሚድኑት ሊሆን ይከጀላል:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 28

وَرَبُّكَ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُ وَيَخۡتَارُۗ مَا كَانَ لَهُمُ ٱلۡخِيَرَةُۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ይመርጣልም:: ለእነርሱ ምርጫ የላቸዉም:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሯቸዉም ላቀ:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 28

وَرَبُّكَ يَعۡلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمۡ وَمَا يُعۡلِنُونَ

69. ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 28

وَهُوَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ لَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلۡأُولَىٰ وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

70. እርሱም አላህ ነው። ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ምስጋና ሁሉ በመጀመሪያም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው:: ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ:: info
التفاسير: