Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Muhammad Ṣādiq

አል-አንዓም

external-link copy
1 : 6

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَۖ ثُمَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ

ምስጋና ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ጨለማዎችንና ብርሃንንም ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ከዚያም እነዚያ የካዱት (ጣዖታትን በጌታቸው) ያስተካክላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 6

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٖ ثُمَّ قَضَىٰٓ أَجَلٗاۖ وَأَجَلٞ مُّسَمًّى عِندَهُۥۖ ثُمَّ أَنتُمۡ تَمۡتَرُونَ

እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም (የሞት) ጊዜን የወሰነ ነው፡፡ እርሱም ዘንድ (ለትንሣኤ) የተወሰነ ጊዜ አልለ፡፡ ከዚያም እናንተ (በመቀስቀሳችሁ) ትጠራጠራላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 6

وَهُوَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ يَعۡلَمُ سِرَّكُمۡ وَجَهۡرَكُمۡ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡسِبُونَ

እርሱም ያ በሰማያትና በምድር (ሊግገዙት የሚገባው) አላህ ነው፡፡ ምስጢራችሁን ግልጻችሁንም ያውቃል፡፡ የምትሠሩትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 6

وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ

ከጌታቸውም አንቀጾች አንዲትም አንቀጽ አትመጣቸውም ከርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 6

فَقَدۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَسَوۡفَ يَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

በእውነቱም (ቁርኣን) በመጣላቸው ጊዜ በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች (ቅጣት) በእርግጥ ይመጣባቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 6

أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ مَّكَّنَّٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَا لَمۡ نُمَكِّن لَّكُمۡ وَأَرۡسَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡهِم مِّدۡرَارٗا وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَنۡهَٰرَ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ

ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንን አላዩምን ለእናንተ ያላስመቸነውን (ለእነርሱ) በምድር ውስጥ አስመቸናቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ዝናምን የተከታተለ ሲኾን ላክን፡፡ ወንዞችንም በሥራቸው እንዲፈሱ አደረግን፡፡ በኃጢአቶቻቸውም አጠፋናቸው፡፡ ከኋላቸውም ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሰዎች አስገኘን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 6

وَلَوۡ نَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ كِتَٰبٗا فِي قِرۡطَاسٖ فَلَمَسُوهُ بِأَيۡدِيهِمۡ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ

ባንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 6

وَقَالُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ مَلَكٞۖ وَلَوۡ أَنزَلۡنَا مَلَكٗا لَّقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ثُمَّ لَا يُنظَرُونَ

«በእርሱም (በሙሐመድ) ላይ መልአክ አይወረድለትም ኖሮአልን» አሉ፡፡ መልአክን ባወረድንም ኖሮ (ባያምኑ በጥፋታቸው) ነገሩ በተፈረደ ነበር፡፡ ከዚያም አይቆዩም ነበር፡፡ info
التفاسير: