क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी

पृष्ठ संख्या:close

external-link copy
80 : 9

ٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ أَوۡ لَا تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ إِن تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ سَبۡعِينَ مَرَّةٗ فَلَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَهُمۡۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ ምሕረትን ብትለምንላቸዉም ወይም ባትለምንላቸው ሁሉም እኩል ነው:: ለእነርሱ ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን አላህ በፍጹም አይምራቸዉምና:: ምክንያቱም እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን አያቀናም:: info
التفاسير:

external-link copy
81 : 9

فَرِحَ ٱلۡمُخَلَّفُونَ بِمَقۡعَدِهِمۡ خِلَٰفَ رَسُولِ ٱللَّهِ وَكَرِهُوٓاْ أَن يُجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَالُواْ لَا تَنفِرُواْ فِي ٱلۡحَرِّۗ قُلۡ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرّٗاۚ لَّوۡ كَانُواْ يَفۡقَهُونَ

81. እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ በኋላ ተገንጥለው በመቀመጣቸው ተደሰቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ:: ለሌሎችም «በሐሩር አትሂዱ» አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የገሀነም እሳት ትኩሳት በጣም ከዚህ የበረታ ነው።» በላቸው:: እናም የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ከዘመቻው አይቀሩም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 9

فَلۡيَضۡحَكُواْ قَلِيلٗا وَلۡيَبۡكُواْ كَثِيرٗا جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

82. አስመሳዮች ጥቂት ጊዜን ብቻ ይሳቁ:: ይሠሩት በነበሩት እኩይ ተግባር ምክንያት ዋጋ ብዙ ጊዜ ያለቅሳሉና:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 9

فَإِن رَّجَعَكَ ٱللَّهُ إِلَىٰ طَآئِفَةٖ مِّنۡهُمۡ فَٱسۡتَـٔۡذَنُوكَ لِلۡخُرُوجِ فَقُل لَّن تَخۡرُجُواْ مَعِيَ أَبَدٗا وَلَن تُقَٰتِلُواْ مَعِيَ عَدُوًّاۖ إِنَّكُمۡ رَضِيتُم بِٱلۡقُعُودِ أَوَّلَ مَرَّةٖ فَٱقۡعُدُواْ مَعَ ٱلۡخَٰلِفِينَ

83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነችው ቡድን አላህ በሰላም ቢመልስህና ካንተ ጋር ዘመቻ ለመውጣት ቢያስፈቅዱህ «ከእኔ ጋር በፍጹም አትወጡም:: ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም:: እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና:: ይልቁንም ከተቀማጮች ጋር ተቀመጡ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 9

وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰٓ أَحَدٖ مِّنۡهُم مَّاتَ أَبَدٗا وَلَا تَقُمۡ عَلَىٰ قَبۡرِهِۦٓۖ إِنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَمَاتُواْ وَهُمۡ فَٰسِقُونَ

84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በሞተ በአንዱም ሰው ላይ ቢሆን ፈጽሞ አትስገድ:: በመቃብሩም ላይ አትቁም:: እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋል:: እነርሱ አመጸኞችም ሆነው ሞተዋልና:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 9

وَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَأَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ

85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚፈልገው በቅርቢቱ ዓለም በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው ሊቀጣቸውና ከሓዲያንም ሆነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ሊያደርግ ብቻ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 9

وَإِذَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٌ أَنۡ ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَجَٰهِدُواْ مَعَ رَسُولِهِ ٱسۡتَـٔۡذَنَكَ أُوْلُواْ ٱلطَّوۡلِ مِنۡهُمۡ وَقَالُواْ ذَرۡنَا نَكُن مَّعَ ٱلۡقَٰعِدِينَ

86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እመኑ:: ከመልዕክተኛው ጋር ሆናችሁ ታገሉ በማለት የቁርኣን ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከእነርሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የሆኑት ሰዎች ለመቅረት ፈቃድ ይጠይቁሃል:: «ከተቀማጮቹ ጋር እንሁን ተወን» ይሉሃል:: info
التفاسير: