क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी

አል ሙጠፊፊን

external-link copy
1 : 83

وَيۡلٞ لِّلۡمُطَفِّفِينَ

1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 83

ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ

2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 83

وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ

3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት):: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 83

أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ

4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
5 : 83

لِيَوۡمٍ عَظِيمٖ

5. ለታላቁ ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 83

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን):: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 83

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٖ

7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ"ሲጂን" ውስጥ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 83

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينٞ

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ሲጂን" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 83

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 83

وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ

10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 83

ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 83

وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ

12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 83

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 83

كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 83

كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّمَحۡجُوبُونَ

15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 83

ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ

16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 83

ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ

17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 83

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ"ዒሊዩን" ውስጥ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 83

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ

19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ዒሊዩን"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
20 : 83

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 83

يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ

21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 83

إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ

22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 83

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 83

تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ

24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 83

يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقٖ مَّخۡتُومٍ

25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 83

خِتَٰمُهُۥ مِسۡكٞۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ

26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 83

وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ

27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 83

عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ

28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 83

إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ

29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 83

وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ

30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 83

وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ

31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 83

وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ

32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- "እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።" ይሉ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 83

وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ

33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 83

فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ

34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 83

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 83

هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ):: info
التفاسير: