क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी

पृष्ठ संख्या:close

external-link copy
22 : 28

وَلَمَّا تَوَجَّهَ تِلۡقَآءَ مَدۡيَنَ قَالَ عَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يَهۡدِيَنِي سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ

22. ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም “ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ” አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 28

وَلَمَّا وَرَدَ مَآءَ مَدۡيَنَ وَجَدَ عَلَيۡهِ أُمَّةٗ مِّنَ ٱلنَّاسِ يَسۡقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ ٱمۡرَأَتَيۡنِ تَذُودَانِۖ قَالَ مَا خَطۡبُكُمَاۖ قَالَتَا لَا نَسۡقِي حَتَّىٰ يُصۡدِرَ ٱلرِّعَآءُۖ وَأَبُونَا شَيۡخٞ كَبِيرٞ

23. ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ እርሱ ላይ ከሰዎች ቡድኖችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ:: ከእነርሱ በታችም ከውሃው መንጎቻቸውን የሚከለክሉ ሁለት ሴቶች ልጆችን አገኘ። “ነገራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን እስከሚመልሱ አናጠጣም። አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው።” አሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 28

فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰٓ إِلَى ٱلظِّلِّ فَقَالَ رَبِّ إِنِّي لِمَآ أَنزَلۡتَ إِلَيَّ مِنۡ خَيۡرٖ فَقِيرٞ

24. ለሁለቱም አጠጣላቸው ከዚያ ወደ ጥላው ዘወር አለና “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደ እኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ” አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 28

فَجَآءَتۡهُ إِحۡدَىٰهُمَا تَمۡشِي عَلَى ٱسۡتِحۡيَآءٖ قَالَتۡ إِنَّ أَبِي يَدۡعُوكَ لِيَجۡزِيَكَ أَجۡرَ مَا سَقَيۡتَ لَنَاۚ فَلَمَّا جَآءَهُۥ وَقَصَّ عَلَيۡهِ ٱلۡقَصَصَ قَالَ لَا تَخَفۡۖ نَجَوۡتَ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

25. ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆና ወደ እርሱ መጣች፤ “አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል” አለችው፤ ወደ እርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ “አትፍራ:: ከበደለኞች ህዝቦች ድነሃል” አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 28

قَالَتۡ إِحۡدَىٰهُمَا يَٰٓأَبَتِ ٱسۡتَـٔۡجِرۡهُۖ إِنَّ خَيۡرَ مَنِ ٱسۡتَـٔۡجَرۡتَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡأَمِينُ

26. ከሁለቱ አንደኛይቱም “አባቴ ሆይ ቅጠረው ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ፤ ብርቱው፤ ታማኙ ነውና” አለችው። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 28

قَالَ إِنِّيٓ أُرِيدُ أَنۡ أُنكِحَكَ إِحۡدَى ٱبۡنَتَيَّ هَٰتَيۡنِ عَلَىٰٓ أَن تَأۡجُرَنِي ثَمَٰنِيَ حِجَجٖۖ فَإِنۡ أَتۡمَمۡتَ عَشۡرٗا فَمِنۡ عِندِكَۖ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أَشُقَّ عَلَيۡكَۚ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

27. “ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶች ልጆቼ አንዲቷን ላጋባህ እሻለሁ፤ ዐስርን ብትሞላም ካንተ ነው:: ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም:: አላህ የሻ እንደሆነ ከመልካም ሰዎች ሆኜ ታገኘኛለህ” አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 28

قَالَ ذَٰلِكَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَۖ أَيَّمَا ٱلۡأَجَلَيۡنِ قَضَيۡتُ فَلَا عُدۡوَٰنَ عَلَيَّۖ وَٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٞ

28. ሙሳም "ይህ ውለታ በእኔና ባንተ መካከል ረጊ ነው:: ከሁለት ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም:: አላህ በምንለው ላይ ሁሉ ምስክር ነው" አለ። info
التفاسير: