क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी

पृष्ठ संख्या:close

external-link copy
72 : 11

قَالَتۡ يَٰوَيۡلَتَىٰٓ ءَأَلِدُ وَأَنَا۠ عَجُوزٞ وَهَٰذَا بَعۡلِي شَيۡخًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عَجِيبٞ

72. እርሷም «ዋልኝ እኔ አሮጊት ይህም ባለቤቴ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው።» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
73 : 11

قَالُوٓاْ أَتَعۡجَبِينَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۖ رَحۡمَتُ ٱللَّهِ وَبَرَكَٰتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِۚ إِنَّهُۥ حَمِيدٞ مَّجِيدٞ

73. «በአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን? :: የአላህ እዝነትና በረከት በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን:: እሱ ምስጉንና ለጋሽ ነውና።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
74 : 11

فَلَمَّا ذَهَبَ عَنۡ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلرَّوۡعُ وَجَآءَتۡهُ ٱلۡبُشۡرَىٰ يُجَٰدِلُنَا فِي قَوۡمِ لُوطٍ

74. ከኢብራሂም ፍራቻው በሄደለትና ብስራት በመጣችለት ጊዜ በሉጥ ህዝቦች ነገር ይከራከረን ጀመር:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 11

إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّٰهٞ مُّنِيبٞ

75. ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፤ አልቃሻ (እጅግ የሚማፀን) እና መላሳ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 11

يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَآۖ إِنَّهُۥ قَدۡ جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَإِنَّهُمۡ ءَاتِيهِمۡ عَذَابٌ غَيۡرُ مَرۡدُودٖ

76. (እነርሱም አሉት): «ኢብራሂም ሆይ! ይህን ክርክር ተው:: እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል:: እነርሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው።» info
التفاسير:

external-link copy
77 : 11

وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗا وَقَالَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَصِيبٞ

77. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ:: ልቡም በእነርሱ ተጨነቀ:: «ይህ ብርቱ ቀን ነዉ።» አለም። info
التفاسير:

external-link copy
78 : 11

وَجَآءَهُۥ قَوۡمُهُۥ يُهۡرَعُونَ إِلَيۡهِ وَمِن قَبۡلُ كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطۡهَرُ لَكُمۡۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ فِي ضَيۡفِيٓۖ أَلَيۡسَ مِنكُمۡ رَجُلٞ رَّشِيدٞ

78. ህዝቦቹም ወደ እርሱ እየተጣደፉ መጡና ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር:: «ህዝቦቼ ሆይ! እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው:: ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው:: አግቧቸው እናም አላህን ፍሩ:: በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ አንድ ቅን ሰው እንኳን የለምን?» አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 11

قَالُواْ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنۡ حَقّٖ وَإِنَّكَ لَتَعۡلَمُ مَا نُرِيدُ

79. «ከሴቶች ልጆችህ እኛ ምንም ጉዳይ የሌለን መሆኑን በትክክል ታውቃለህ:: አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 11

قَالَ لَوۡ أَنَّ لِي بِكُمۡ قُوَّةً أَوۡ ءَاوِيٓ إِلَىٰ رُكۡنٖ شَدِيدٖ

80. «በእናንተ ላይ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 11

قَالُواْ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓاْ إِلَيۡكَۖ فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٌ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَۖ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمۡۚ إِنَّ مَوۡعِدَهُمُ ٱلصُّبۡحُۚ أَلَيۡسَ ٱلصُّبۡحُ بِقَرِيبٖ

81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት። info
التفاسير: