કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

አል አዕላ

external-link copy
1 : 87

سَبِّحِ ٱسۡمَ رَبِّكَ ٱلۡأَعۡلَى

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አጥራ (አሞግስ)። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 87

ٱلَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ

2. ያ ሁሉን ነገር የፈጠረውንና ያስተካከለውን፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 87

وَٱلَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ

3. ያን የወሰነውን ነገርንም ሁሉ ለተፈጠረለት የመራውን፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 87

وَٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلۡمَرۡعَىٰ

4. ያም ግጦሽን ለምለም አርጎ ያወጣውን፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 87

فَجَعَلَهُۥ غُثَآءً أَحۡوَىٰ

5.(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 87

سَنُقۡرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰٓ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፤ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 87

إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ وَمَا يَخۡفَىٰ

7. አላህ ከፈለገው ነገር በስተቀር፤ እናም እርሱ ግልጹንም የሚሸሽገውንም ሁሉ ያውቃልና፤ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 87

وَنُيَسِّرُكَ لِلۡيُسۡرَىٰ

8. ለገሪቱም (ሕይወት እስላምን ትከተል ዘንድ) እናገራሃለን። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 87

فَذَكِّرۡ إِن نَّفَعَتِ ٱلذِّكۡرَىٰ

9. (ሰዎችንም) ገስፅ፤ ግሳፄይቱ ብትጠቅም። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 87

سَيَذَّكَّرُ مَن يَخۡشَىٰ

10. (አላህን) የሚፈራ በእርግጥ ይገሰፃል። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 87

وَيَتَجَنَّبُهَا ٱلۡأَشۡقَى

11. መናጢዉም ይርቃታል:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 87

ٱلَّذِي يَصۡلَى ٱلنَّارَ ٱلۡكُبۡرَىٰ

12. ያ! ታላቂቱን እሳት የሚገባው፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 87

ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ

13. ከዚያም በእርሷ ውስጥ የማይሞትና ህያዉም የማይሆነው። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 87

قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ

14. (አላህን ከማመፅ) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፤ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 87

وَذَكَرَ ٱسۡمَ رَبِّهِۦ فَصَلَّىٰ

15. የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 87

بَلۡ تُؤۡثِرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا

16. ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ታስቀድማላችሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 87

وَٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓ

17. (ሰዎች ሆይ!) መጨረሻይቱ ሕይወት በላጭና፤ ዘወታሪ ሆና ሳለ። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 87

إِنَّ هَٰذَا لَفِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ

18. ይህ በቀደምቶቹም መጻሕፍት ውስጥ ያለ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 87

صُحُفِ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ

19. በኢብራሂምና በሙሳ መጽሐፍት ውስጥ የሰፈረ እውነታ ነው። info
التفاسير: