કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
46 : 8

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَٰزَعُواْ فَتَفۡشَلُواْ وَتَذۡهَبَ رِيحُكُمۡۖ وَٱصۡبِرُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ

46. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ :: አትጨቃጨቁም ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትሄዳለችና:: ታገሡም አላህ በእርዳታው ከትዕግሥተኞች ጋር ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 8

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِم بَطَرٗا وَرِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ

47. እንደ እነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከሀገራቸው እንደወጡት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በሚሠሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 8

وَإِذۡ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّي جَارٞ لَّكُمۡۖ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلۡفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ وَقَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكُمۡ إِنِّيٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوۡنَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَۚ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

48. ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም:: እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ።» ባለ ጊዜም (የሆነውን አስታውስ):: ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ ወደኋላው አፈገፈገ:: «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ:: እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ:: እኔ አላህን እፈራለሁ:: አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው።» አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 8

إِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَٰٓؤُلَآءِ دِينُهُمۡۗ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች «እነዚህን ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው አታለላቸው።» ባሉ ጊዜ (የነበረውን አስታውስ):: በአላህ ላይ የሚጠጋ (ሁልጊዜም ያሸንፋል):: አላህ ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 8

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ የካዱትን ሰዎች መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎን ስቃይ ቅመሱ።» እያሉ በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር):: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 8

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ

51. «ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህ ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
52 : 8

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

52. የእነዚያ ሰዎች ልማድ እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ህዝቦች ልማድ ነው:: በአላህ አናቅጽ ካዱ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው:: አላህ ሀይለኛና ቅጣተ ብርቱ ነውና:: info
التفاسير: