કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
148 : 4

۞ لَّا يُحِبُّ ٱللَّهُ ٱلۡجَهۡرَ بِٱلسُّوٓءِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ إِلَّا مَن ظُلِمَۚ وَكَانَ ٱللَّهُ سَمِيعًا عَلِيمًا

148. አላህ በክፉ ንግግር መጮህን ከተበደለ ሰው ጩኸት በስተቀር አይወድም:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
149 : 4

إِن تُبۡدُواْ خَيۡرًا أَوۡ تُخۡفُوهُ أَوۡ تَعۡفُواْ عَن سُوٓءٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوّٗا قَدِيرًا

149. ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (በደል) ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ እና ቻይ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
150 : 4

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡفُرُونَ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُواْ بَيۡنَ ٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيَقُولُونَ نُؤۡمِنُ بِبَعۡضٖ وَنَكۡفُرُ بِبَعۡضٖ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُواْ بَيۡنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا

150. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ የሚክዱ፤ በአላህና በመልዕክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉና «በከፊሉ እናምናለን በከፊሉ ደግሞ እንክዳለን» የሚሉ ሁሉ በዚህ መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፣ info
التفاسير:

external-link copy
151 : 4

أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ حَقّٗاۚ وَأَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا

151. በእውነቱ እነዚያ ከሓዲያን እነርሱው ናቸው:: ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል:: info
التفاسير:

external-link copy
152 : 4

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَلَمۡ يُفَرِّقُواْ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّنۡهُمۡ أُوْلَٰٓئِكَ سَوۡفَ يُؤۡتِيهِمۡ أُجُورَهُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

152. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ፤ ከእነርሱም መካከል በአንዱም ያልለዩ ሰዎች እነዚያ ምንዳዎቻቸው በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
153 : 4

يَسۡـَٔلُكَ أَهۡلُ ٱلۡكِتَٰبِ أَن تُنَزِّلَ عَلَيۡهِمۡ كِتَٰبٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِۚ فَقَدۡ سَأَلُواْ مُوسَىٰٓ أَكۡبَرَ مِن ذَٰلِكَ فَقَالُوٓاْ أَرِنَا ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ بِظُلۡمِهِمۡۚ ثُمَّ ٱتَّخَذُواْ ٱلۡعِجۡلَ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ فَعَفَوۡنَا عَن ذَٰلِكَۚ وَءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينٗا

153. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል:: ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል:: «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል:: በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው:: ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድረገው ያዙ:: ከዚያ ያንን ይቅር አልን:: ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው:: info
التفاسير:

external-link copy
154 : 4

وَرَفَعۡنَا فَوۡقَهُمُ ٱلطُّورَ بِمِيثَٰقِهِمۡ وَقُلۡنَا لَهُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡبَابَ سُجَّدٗا وَقُلۡنَا لَهُمۡ لَا تَعۡدُواْ فِي ٱلسَّبۡتِ وَأَخَذۡنَا مِنۡهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا

154. በቃል ኪዳናቸው ምክንያት የጡር ተራራን ከበላያቸው አነሳን:: ለእነርሱም «ደጃፍን ስትገቡ አጎንብሳችሁ ግቡ።» አልን:: ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላለፉ።» አልን:: ከእነርሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን:: info
التفاسير: