કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર: 17:2 close

external-link copy
113 : 2

وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ لَيۡسَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ لَيۡسَتِ ٱلۡيَهُودُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَهُمۡ يَتۡلُونَ ٱلۡكِتَٰبَۗ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ مِثۡلَ قَوۡلِهِمۡۚ فَٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

113. እነርሱ መጽሐፉን የሚያነቡ ሲሆን አይሁድ «ክርስቲያኖች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አይሁዶች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ። እንደዚሁ እነዚያ የማያውቁት አጋሪዎችም የነሱን ተመሳሳይ ንግግር ተናገሩ:: አላህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ላይ ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
114 : 2

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ أَن يُذۡكَرَ فِيهَا ٱسۡمُهُۥ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَآۚ أُوْلَٰٓئِكَ مَا كَانَ لَهُمۡ أَن يَدۡخُلُوهَآ إِلَّا خَآئِفِينَۚ لَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا خِزۡيٞ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٞ

114. የአላህን መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳበት ከከለከለና መስጊዶችንም ለማበላሸት ከጣረ ይበልጥ ድንበር አላፊ (አጥፊ) ማን ነው? እነዚያ በፍርሃት ተውጠው እንጂ ወደ መስጊዶች ሊገቡ አይገባቸዉም። ለነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: በመጨረሻይቱ ሀገርም ታላቅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
115 : 2

وَلِلَّهِ ٱلۡمَشۡرِقُ وَٱلۡمَغۡرِبُۚ فَأَيۡنَمَا تُوَلُّواْ فَثَمَّ وَجۡهُ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ وَٰسِعٌ عَلِيمٞ

115. ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ብቻ ነው:: በአላህ ትእዛዝ (ፊቶቻችሁን) ለሶላት ወደ የትም አቅጣጫ ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ዘንድ ነው:: አላህ በእርግጥ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነዉና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
116 : 2

وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۖ بَل لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ كُلّٞ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ

116. አላህ «ልጅ አለው።» አሉ:: ከሚሉት ጥራት ተገባው:: ይልቁንም በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
117 : 2

بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَإِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

117. ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው:: ማንንም ነገር ማስገኘት በፈለገ ጊዜ ለእርሱ የሚለው ‹‹ሁን›› ብቻ ነው:: ወዲያዉም እንዳለው ይሆናል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
118 : 2

وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ لَوۡلَا يُكَلِّمُنَا ٱللَّهُ أَوۡ تَأۡتِينَآ ءَايَةٞۗ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِم مِّثۡلَ قَوۡلِهِمۡۘ تَشَٰبَهَتۡ قُلُوبُهُمۡۗ قَدۡ بَيَّنَّا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يُوقِنُونَ

118. እነዚያ የማያውቁት «(አንተ መልዕክተኛ ስለመሆንህ) አላህ ለምን አያናግረንም? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ተዓምር አይመጣልንም ኖሯልን? አሉ:: እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚሁ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል:: ልቦቻቸው በክህደት ተመሳሰሉ:: ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን በእርግጥ አብራርተናል:: info
التفاسير:

external-link copy
119 : 2

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗاۖ وَلَا تُسۡـَٔلُ عَنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡجَحِيمِ

119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነት ላክንህ:: ከእሳት ጓዶችም ሁኔታ አትጠየቅም፡፡ info
التفاسير: