કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

external-link copy
97 : 17

وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُمۡ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِهِۦۖ وَنَحۡشُرُهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ عُمۡيٗا وَبُكۡمٗا وَصُمّٗاۖ مَّأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ كُلَّمَا خَبَتۡ زِدۡنَٰهُمۡ سَعِيرٗا

97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው:: እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም:: የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን:: info
التفاسير: