Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik

external-link copy
61 : 2

وَإِذۡ قُلۡتُمۡ يَٰمُوسَىٰ لَن نَّصۡبِرَ عَلَىٰ طَعَامٖ وَٰحِدٖ فَٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ يُخۡرِجۡ لَنَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلۡأَرۡضُ مِنۢ بَقۡلِهَا وَقِثَّآئِهَا وَفُومِهَا وَعَدَسِهَا وَبَصَلِهَاۖ قَالَ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِي هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِي هُوَ خَيۡرٌۚ ٱهۡبِطُواْ مِصۡرٗا فَإِنَّ لَكُم مَّا سَأَلۡتُمۡۗ وَضُرِبَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلذِّلَّةُ وَٱلۡمَسۡكَنَةُ وَبَآءُو بِغَضَبٖ مِّنَ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَانُواْ يَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقۡتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۚ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَواْ وَّكَانُواْ يَعۡتَدُونَ

61. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! በአንድ ዓይነት ምግብ ላይ በፍጹም አንታገስም:: ስለዚህ ጌታህ ከእነዚያ ምድር ከምታበቅላቸው ከቅጠላ ቅጠሏ፤ ከዱባዋ፤ ከስንዴዋ፤ ከምስሯና ከሽንኩርቷ ያወጣልን ዘንድ ለምንልን።» (ባላችሁም ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ):: ሙሳም «ያንን ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ ከፍተኛና በላጭ በሆነው ነገር ልትተኩ ትፈልጋላችሁን? ወደ ከተማ ውረዱ:: የጠየቃችሁትን ነገር ታገኛላችሁና።» አላቸው። ውርደትና ድህነት ተጣለባቸው:: በአላህም ቁጣ ተመለሱ:: ይህ እነርሱ በአላህ ተዐምራት ይክዱና ነብያትንም ያለ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ፤ በኃጢአትም ላይ በመዘፈቃቸውና እንዲሁም ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው። info
التفاسير: