Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik

external-link copy
219 : 2

۞ يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡخَمۡرِ وَٱلۡمَيۡسِرِۖ قُلۡ فِيهِمَآ إِثۡمٞ كَبِيرٞ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَإِثۡمُهُمَآ أَكۡبَرُ مِن نَّفۡعِهِمَاۗ وَيَسۡـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَۖ قُلِ ٱلۡعَفۡوَۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَتَفَكَّرُونَ

219. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዕምሮን ስለሚያሰክር መጠጥና ስለ ቁማር ይጠይቁሃል:: «በሁለቱም ትልቅ ኃጢአትነትና ለሰዎችም ጥቅም አለባቸው:: ኃጢአታቸው ግን ከጥቅማቸው በጣም የገዘፈ ነው።» በላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሀል:: «የተረፋችሁን መጽውቱ።» በላቸው:: እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ info
التفاسير: