ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا

አል ጁሙዓህ

external-link copy
1 : 62

يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡمَلِكِ ٱلۡقُدُّوسِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

1. በሰማይና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ንጉስ፤ ፍፁም (ከጉድለት ንጹህ)፤ አሸናፊና ጥበበኛ የሆነውን አላህን ያሞግሳል:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 62

هُوَ ٱلَّذِي بَعَثَ فِي ٱلۡأُمِّيِّـۧنَ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمۡ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلُ لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

2. እርሱ ያ ለመሃይማን ዐረቦች የቁርአን አናቅጽን በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፤ የሚያጠራቸዉም፤ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉም የሆነን መልዕክተኛ ሙሐመድን ከእነርሱ መካከል የላከ ነው:: እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 62

وَءَاخَرِينَ مِنۡهُمۡ لَمَّا يَلۡحَقُواْ بِهِمۡۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

3.ከነሱም ሌሎችም ገና ያልተከተሏቸው በሆኑት ላይ የላከው ነው:: እርሱም አሸናፊና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 62

ذَٰلِكَ فَضۡلُ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ

4. ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 62

مَثَلُ ٱلَّذِينَ حُمِّلُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ ثُمَّ لَمۡ يَحۡمِلُوهَا كَمَثَلِ ٱلۡحِمَارِ يَحۡمِلُ أَسۡفَارَۢاۚ بِئۡسَ مَثَلُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

5. የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያ ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ ልክ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው:: የእነዚያ በአላህ አናቅጽ ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ:: አላህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 62

قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ هَادُوٓاْ إِن زَعَمۡتُمۡ أَنَّكُمۡ أَوۡلِيَآءُ لِلَّهِ مِن دُونِ ٱلنَّاسِ فَتَمَنَّوُاْ ٱلۡمَوۡتَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ አይሁዳውያን ሆይ! ከሰው ሁሉ በተለየ እናንተ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉና በዚያ አባባላችሁ እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 62

وَلَا يَتَمَنَّوۡنَهُۥٓ أَبَدَۢا بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ

7. እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም:: አላህ በዳዮችን አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 62

قُلۡ إِنَّ ٱلۡمَوۡتَ ٱلَّذِي تَفِرُّونَ مِنۡهُ فَإِنَّهُۥ مُلَٰقِيكُمۡۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው:: ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ወደ ሆነው ጌታ በቂያማ ዕለት ተመላሾች ናችሁ:: ትሰሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው:: info
التفاسير: