ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا

አድ ዱኻን

external-link copy
1 : 44

حمٓ

1. ሓ፤ ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 44

وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ

2. ሁሉን ነገር አብራሪ በሆነው መጽሐፍ እንምላለን:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 44

إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ فِي لَيۡلَةٖ مُّبَٰرَكَةٍۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ

3. እኛ ቁርኣኑን በዚያች በተባረከችው ሌሊት ውስጥ አወረድነው:: እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 44

فِيهَا يُفۡرَقُ كُلُّ أَمۡرٍ حَكِيمٍ

4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይለያል:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 44

أَمۡرٗا مِّنۡ عِندِنَآۚ إِنَّا كُنَّا مُرۡسِلِينَ

5. ከእኛ ዘንድ የሆነ ትዕዛዝ ሲሆን አወረድነው:: እኛ መልዕክተኞችን ላኪዎች ነበርንና:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 44

رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

6. (መልዕክተኞች) ከጌታህ በሆነው ችሮታ (ተላኩ)። እነሆ እርሱ(አላህ) የሚባለዉን ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 44

رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ

7. የሰማያት፤ የምድር እና በመካከላቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ ጌታ ከሆነው (ተላኩ)። የምታረጋግጡ እንደሆናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መሆኑን እወቁ):: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 44

لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ رَبُّكُمۡ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ

8. ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። ህያው ያደርጋል። ህይወትም ይነሳል። ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 44

بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ يَلۡعَبُونَ

9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲሆኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 44

فَٱرۡتَقِبۡ يَوۡمَ تَأۡتِي ٱلسَّمَآءُ بِدُخَانٖ مُّبِينٖ

10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ( ሰዎችን) የሚሸፍን በሆነ ግልጽ ጭስ ሰማይ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 44

يَغۡشَى ٱلنَّاسَۖ هَٰذَا عَذَابٌ أَلِيمٞ

11.ሰዎችን ይሸፍናል ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 44

رَّبَّنَا ٱكۡشِفۡ عَنَّا ٱلۡعَذَابَ إِنَّا مُؤۡمِنُونَ

12. ጌታችን ሆይ! ክእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን:: እኛ ትክክለኛ አማኞች ነንና (ይላሉ::) info
التفاسير:

external-link copy
13 : 44

أَنَّىٰ لَهُمُ ٱلذِّكۡرَىٰ وَقَدۡ جَآءَهُمۡ رَسُولٞ مُّبِينٞ

13. አስረጂ መልዕክተኛ የመጣላቸው እና በአላህ የካዱ ሲሆኑ (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? info
التفاسير:

external-link copy
14 : 44

ثُمَّ تَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ وَقَالُواْ مُعَلَّمٞ مَّجۡنُونٌ

14. ከዚያም «ከሰው የተስተማረ እብድ ነው» ያሉ ሲሆኑ ከእርሱ ዞሩ። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 44

إِنَّا كَاشِفُواْ ٱلۡعَذَابِ قَلِيلًاۚ إِنَّكُمۡ عَآئِدُونَ

15. እኛ ቅጣትን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን። እናንተ ግን ወደ ክህደታችሁ በእርግጥ አንደገና ተመላሾች ናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 44

يَوۡمَ نَبۡطِشُ ٱلۡبَطۡشَةَ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ إِنَّا مُنتَقِمُونَ

16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን እኛ ተበቃዮች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 44

۞ وَلَقَدۡ فَتَنَّا قَبۡلَهُمۡ قَوۡمَ فِرۡعَوۡنَ وَجَآءَهُمۡ رَسُولٞ كَرِيمٌ

17. ከእነርሱ በፊት የፈርዖንን ህዝቦች በእርግጥ ሞከርን:: ክቡር መልዕክተኛም መጣላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 44

أَنۡ أَدُّوٓاْ إِلَيَّ عِبَادَ ٱللَّهِۖ إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ

18. «የአላህን ባሮች ወደ እኔ አድርሱ (ለኔ ስጡኝ):: እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝና። info
التفاسير: