ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا

شماره صفحه:close

external-link copy
21 : 41

وَقَالُواْ لِجُلُودِهِمۡ لِمَ شَهِدتُّمۡ عَلَيۡنَاۖ قَالُوٓاْ أَنطَقَنَا ٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَنطَقَ كُلَّ شَيۡءٖۚ وَهُوَ خَلَقَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

21. ለቆዳዎቻቸዉም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ። «ያ ሁሉን ነገር ያናገረው አላህ አናገረን:: እርሱም (ነው) በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ። ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 41

وَمَا كُنتُمۡ تَسۡتَتِرُونَ أَن يَشۡهَدَ عَلَيۡكُمۡ سَمۡعُكُمۡ وَلَآ أَبۡصَٰرُكُمۡ وَلَا جُلُودُكُمۡ وَلَٰكِن ظَنَنتُمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَا يَعۡلَمُ كَثِيرٗا مِّمَّا تَعۡمَلُونَ

22. ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁ በእናንተ ላይ እንዳይመሰክሩባችሁ የምትደበቁባቸው አልነበራችሁም:: ግን አላህ ከምትሰሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 41

وَذَٰلِكُمۡ ظَنُّكُمُ ٱلَّذِي ظَنَنتُم بِرَبِّكُمۡ أَرۡدَىٰكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم مِّنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

23. ይህም ለጌታችሁ የጠረጣችሁት ጥርጣሬያችሁ አጠፋችሁ:: ከከሳሪዎችም ሆናችሁ ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 41

فَإِن يَصۡبِرُواْ فَٱلنَّارُ مَثۡوٗى لَّهُمۡۖ وَإِن يَسۡتَعۡتِبُواْ فَمَا هُم مِّنَ ٱلۡمُعۡتَبِينَ

24. ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት:: ወደ ሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 41

۞ وَقَيَّضۡنَا لَهُمۡ قُرَنَآءَ فَزَيَّنُواْ لَهُم مَّا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَحَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلُ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ خَٰسِرِينَ

25. ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው:: በፊታቸውን ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው:: ከአጋንንትና ከሰዉም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው:: እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 41

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَسۡمَعُواْ لِهَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ وَٱلۡغَوۡاْ فِيهِ لَعَلَّكُمۡ تَغۡلِبُونَ

26. እነዚያም «በአላህ የካዱት ሰዎች ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብም ተንጫጩበት።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 41

فَلَنُذِيقَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَذَابٗا شَدِيدٗا وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَسۡوَأَ ٱلَّذِي كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

27. እነዚያንም በአላህ የካዱትን ብርቱ ቅጣት እናቀምሳቸዋለን:: የእነዚያንም ይሰሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ እንመነዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 41

ذَٰلِكَ جَزَآءُ أَعۡدَآءِ ٱللَّهِ ٱلنَّارُۖ لَهُمۡ فِيهَا دَارُ ٱلۡخُلۡدِ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ

28. ይህ የአላህ ጠላቶች ፍዳ እሳት ነው:: በውስጧም ለእነርሱ የዘላለም መኖሪያ አገር አላቸው:: በአንቀፆቻቸን ይክዱ በነበሩት ምንዳ ይመነዳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 41

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ رَبَّنَآ أَرِنَا ٱلَّذَيۡنِ أَضَلَّانَا مِنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ نَجۡعَلۡهُمَا تَحۡتَ أَقۡدَامِنَا لِيَكُونَا مِنَ ٱلۡأَسۡفَلِينَ

29. እነዚያም በአላህ የካዱት በእሳት ውስጥ ሆነው «ጌታችን ሆይ! እነዚያ ከአጋንንትና ከሰው ያሳሳቱንን አሳየን። ከታችኞች ይሆኑ ዘንድ ከጫማዎቻችን ስር እናደርጋቸዋለንና» ይላሉ:: info
التفاسير: