ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهاری - محمد صادق

አል በለድ

external-link copy
1 : 90

لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ

በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 90

وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ

አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 90

وَوَالِدٖ وَمَا وَلَدَ

በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 90

لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ

ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 90

أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدٞ

በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? info
التفاسير:

external-link copy
6 : 90

يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالٗا لُّبَدًا

«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 90

أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ

አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? info
التفاسير:

external-link copy
8 : 90

أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ

ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 90

وَلِسَانٗا وَشَفَتَيۡنِ

ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 90

وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ

ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? info
التفاسير:

external-link copy
11 : 90

فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ

ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 90

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ

ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 90

فَكُّ رَقَبَةٍ

(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 90

أَوۡ إِطۡعَٰمٞ فِي يَوۡمٖ ذِي مَسۡغَبَةٖ

ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 90

يَتِيمٗا ذَا مَقۡرَبَةٍ

የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 90

أَوۡ مِسۡكِينٗا ذَا مَتۡرَبَةٖ

ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 90

ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ

ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 90

أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ

እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 90

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ

እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 90

عَلَيۡهِمۡ نَارٞ مُّؤۡصَدَةُۢ

በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ info
التفاسير: