আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
37 : 9

إِنَّمَا ٱلنَّسِيٓءُ زِيَادَةٞ فِي ٱلۡكُفۡرِۖ يُضَلُّ بِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُحِلُّونَهُۥ عَامٗا وَيُحَرِّمُونَهُۥ عَامٗا لِّيُوَاطِـُٔواْ عِدَّةَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ فَيُحِلُّواْ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُۚ زُيِّنَ لَهُمۡ سُوٓءُ أَعۡمَٰلِهِمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ

37. የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ ክህደትን መጨመር ነው:: በዚህ ተግባር ላይ እነዚያ በአላህ የካዱት (ሰዎች) ይሳሳቱበታል:: በአንደኛው ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል:: በሌላው ዓመት ደግሞ ያወግዙታል:: ይህም አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊሞሉበትና አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ የተፈቀደ ሊያደርጉበት ነው:: መጥፎ ሥራዎቻቸው ለእነርሱ ተዋበላቸው:: አላህ ከሓዲያን ህዝቦችን ወደ ቀናው መንገድ አይመራም:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 9

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَا لَكُمۡ إِذَا قِيلَ لَكُمُ ٱنفِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱثَّاقَلۡتُمۡ إِلَى ٱلۡأَرۡضِۚ أَرَضِيتُم بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مِنَ ٱلۡأٓخِرَةِۚ فَمَا مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا قَلِيلٌ

38. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! «በአላህ መንገድ ለመታገል ዝመቱ።» በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለምንድን ነው? የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ ወደዳችሁን? የቅርቢቱ ህይወት ጥቅም ከመጨረሻይቱ ህይወት አንፃር ጥቂት እንጂ ምንም አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 9

إِلَّا تَنفِرُواْ يُعَذِّبۡكُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا وَيَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّوهُ شَيۡـٔٗاۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

39. ( አማኞች ሆይ!) ለዘመቻ ባትወጡ አላህ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል:: ከናንተ ሌላ የሆኑን ህዝቦችም ይለውጣል:: አላህን በምንም አትጎዱትምም:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 9

إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدۡ نَصَرَهُ ٱللَّهُ إِذۡ أَخۡرَجَهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ثَانِيَ ٱثۡنَيۡنِ إِذۡ هُمَا فِي ٱلۡغَارِ إِذۡ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحۡزَنۡ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَاۖ فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَيۡهِ وَأَيَّدَهُۥ بِجُنُودٖ لَّمۡ تَرَوۡهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلسُّفۡلَىٰۗ وَكَلِمَةُ ٱللَّهِ هِيَ ٱلۡعُلۡيَاۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ነብዩ ሙሐመድን ባትረዱት እነዚያ በአላህ የካዱት ህዝቦች የሁለት ሰዎች ሁለተኛ ሆኖ ከመካ ባስወጡት ጊዜ አላህ ረድቶታል:: ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው «አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና» ባለ ጊዜ አላህ እርጋታውን በእርሱ ላይ አወረደ:: ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው:: የእነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች ቃል የበታች አደረገ:: የአላህ ቃል ግን የበላይ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير: