আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
53 : 8

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمۡ يَكُ مُغَيِّرٗا نِّعۡمَةً أَنۡعَمَهَا عَلَىٰ قَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ

53. ይህ ቅጣት አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመሆኑ ምክንያት ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 8

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَۚ وَكُلّٞ كَانُواْ ظَٰلِمِينَ

54. እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያ ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸዉም)። በጌታቸው ታዓምራት አስተባበሉና በኃጢአቶቻቸው አጠፋናቸው:: የፈርዖንን ቤተሰቦች አስመጥናቸው:: ሁሉም በዳዮች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 8

إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

55. ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ የካዱት ሰዎች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 8

ٱلَّذِينَ عَٰهَدتَّ مِنۡهُمۡ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهۡدَهُمۡ فِي كُلِّ مَرَّةٖ وَهُمۡ لَا يَتَّقُونَ

56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከእነርሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸውና ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው:: እነርሱም አይጠነቀቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 8

فَإِمَّا تَثۡقَفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡحَرۡبِ فَشَرِّدۡ بِهِم مَّنۡ خَلۡفَهُمۡ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ

57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦር ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት ሌሎቹ ከሓዲያን ይገሠጡ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 8

وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوۡمٍ خِيَانَةٗ فَٱنۢبِذۡ إِلَيۡهِمۡ عَلَىٰ سَوَآءٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡخَآئِنِينَ

58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦችም በኩል ክህደትን ብትፈራ የቃል ኪዳኑን መፍረስ በማወቅ በኩል ተመሳሳይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደ እነርሱ ጣልላቸው:: አላህ ከዳተኞችን ሁሉ አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 8

وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَبَقُوٓاْۚ إِنَّهُمۡ لَا يُعۡجِزُونَ

59. እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መሆናቸውን አያስቡ:: እነርሱ አያቅቱምና (አያሸንፉምና):: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 8

وَأَعِدُّواْ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةٖ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَيۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ وَءَاخَرِينَ مِن دُونِهِمۡ لَا تَعۡلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ يَعۡلَمُهُمۡۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِن شَيۡءٖ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ

60. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ለእነርሱ ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶች የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በስተቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ ብቻ የሚያውቃቸውን አስመሳዮች የምታሸብሩበት ስትሆኑ አዘጋጁላቸው:: ከማንኛዉም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱት ምንዳው ወደ እናንተ በሙሉ ይሰጣል:: እናንተ ቅንጣት አትበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
61 : 8

۞ وَإِن جَنَحُواْ لِلسَّلۡمِ فَٱجۡنَحۡ لَهَا وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዕርቅ ቢያዘነብሉ አንተም ወደ እርቁ ተዘንበልና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂው ነውና። info
التفاسير: