আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

አል ቂያማህ

external-link copy
1 : 75

لَآ أُقۡسِمُ بِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ

1. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በትንሳኤ ቀን እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 75

وَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ

2. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 75

أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجۡمَعَ عِظَامَهُۥ

3. (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ።) ሰው አጥንቶችን ለመሰብሰባችን ይጠራጠራልን? info
التفاسير:

external-link copy
4 : 75

بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُۥ

4. እንዴታ ጣቶቹንም ፊት እንደነበሩት በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 75

بَلۡ يُرِيدُ ٱلۡإِنسَٰنُ لِيَفۡجُرَ أَمَامَهُۥ

5. ይልቁን ሰው በፊቱ ባለ ነገር በትንሳኤ ቀን ሊያስተባብል ይፈልጋል:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 75

يَسۡـَٔلُ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلۡقِيَٰمَةِ

6. «የትንሳኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 75

فَإِذَا بَرِقَ ٱلۡبَصَرُ

7. ዓይንም በዋለለ ጊዜ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 75

وَخَسَفَ ٱلۡقَمَرُ

8. ጨረቃም በጨለመ ጊዜ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 75

وَجُمِعَ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ

9. ጸሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 75

يَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذٍ أَيۡنَ ٱلۡمَفَرُّ

10. ሰው በዚያን ቀን «መሸሻው የት ነው?» ይላል። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 75

كَلَّا لَا وَزَرَ

11. «ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 75

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمُسۡتَقَرُّ

12. በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።» ይባላል። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 75

يُنَبَّؤُاْ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذِۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ

13. ሰው በዚያን ቀን ያስቀደመውም ያስቆየውም ሁሉ ይነገረዋል። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 75

بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٞ

14. በእርግጥ ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 75

وَلَوۡ أَلۡقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ

15. ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣ እንኳን (አይሰማም)። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 75

لَا تُحَرِّكۡ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعۡجَلَ بِهِۦٓ

16. በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ብለህ ምላስህን አታላውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 75

إِنَّ عَلَيۡنَا جَمۡعَهُۥ وَقُرۡءَانَهُۥ

17. በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማስነበቡ በኛ ላይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 75

فَإِذَا قَرَأۡنَٰهُ فَٱتَّبِعۡ قُرۡءَانَهُۥ

18. ባነበብነው ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 75

ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا بَيَانَهُۥ

19. ከዚያም (ላንተ) ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 75

كَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ

20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጣደፍ ተከልከል፤ ይልቁንም (ሰዎች ስትባሉ) ፈጣኒቱን ዓለም ትወዳላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 75

وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ

21. የመጨረሻይቱን ዓለም (ግን) ትተዋላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 75

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاضِرَةٌ

22. (የተወሰኑ) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 75

إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٞ

23. ወደ ጌታቸው ተመልካቾችም ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 75

وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٞ

24. (ሌሎች) ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን አጨፍጋጊዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 75

تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٞ

25. በእነርሱም ላይ አደጋ እንደሚሰራባቸው ያረጋገጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 75

كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ

26. (ሙስሊሞች አስተውሉ።) (ነፍስ) ወደ ጉሮሮ በደረሰች፤ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 75

وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٖ

27. «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 75

وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ

28. (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 75

وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ

29. ባትም ከባት በተጣበቀች ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 75

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ

30. በዚያ ቀን መነዳት ወደ ጌታህ (ፍርድ) ብቻ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 75

فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ

31. እናም (ከሀዲው) አላመነምም፤ አልሰገደምም። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 75

وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ

32. ግን በአላህ አስተባበለ፤ ከእምነት ዞረም:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 75

ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ

33. ከዚያም እየተንጎማለለ ወደ ቤተሰቡ ሄደ። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 75

أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ

34. (የምትጠላውን ነገር) ላንተው ይሁን፤ ላንተ ተገቢህም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 75

ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ

35. ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ላንተ የተገባህም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 75

أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى

36. ሰው እንደፈለገ እንዲኖር ልቅ ሆኖ የሚተው ይመስለዋልን? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 75

أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةٗ مِّن مَّنِيّٖ يُمۡنَىٰ

37. የሚፈስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 75

ثُمَّ كَانَ عَلَقَةٗ فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ

38. ከዚያ የረጋ ደም ሆነ:: ከዚያ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠረው፤ አስተካከለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 75

فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ

39. ከእርሱም ሁለት ዓይነቶች ወንድና ሴትን አደረገ። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 75

أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ

40. (ታዲያ) ይህ ሀያል (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን? info
التفاسير: