আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
4 : 59

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۖ وَمَن يُشَآقِّ ٱللَّهَ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

4. ይህ እነርሱ አላህንና መልዕክተኛውን በመከራከራቸው ምክንያት ነው:: አላህን የሚከራከር ሰው ሁሉ (ይቀጣዋል።) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና ይቀጣቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 59

مَا قَطَعۡتُم مِّن لِّينَةٍ أَوۡ تَرَكۡتُمُوهَا قَآئِمَةً عَلَىٰٓ أُصُولِهَا فَبِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَلِيُخۡزِيَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

5. ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ሆና የተዋችኋት ሁሉ በአላህ ፈቃድ ነው:: አመጸኞችንም ያዋርድ ዘንድ (መቁረጥን ፈቀደ):: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 59

وَمَآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡهُمۡ فَمَآ أَوۡجَفۡتُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ خَيۡلٖ وَلَا رِكَابٖ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُسَلِّطُ رُسُلَهُۥ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

6. ከእነርሱም ገንዘብ ወደ መልዕክተኛው አላህ የመለሰውን በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋልባችሁበትም:: ግን አላህ መልዕክተኞቹን በሚሻው ላይ ይሾማል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 59

مَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ كَيۡ لَا يَكُونَ دُولَةَۢ بَيۡنَ ٱلۡأَغۡنِيَآءِ مِنكُمۡۚ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمۡ عَنۡهُ فَٱنتَهُواْۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

7. አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው:: መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት:: የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ:: አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 59

لِلۡفُقَرَآءِ ٱلۡمُهَٰجِرِينَ ٱلَّذِينَ أُخۡرِجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَأَمۡوَٰلِهِمۡ يَبۡتَغُونَ فَضۡلٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٗا وَيَنصُرُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ

8. ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉና አላህንና መልዕክተኛውን የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡ (ለተባረሩ) ስደተኞች ድሆች ይሰጣል:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 59

وَٱلَّذِينَ تَبَوَّءُو ٱلدَّارَ وَٱلۡإِيمَٰنَ مِن قَبۡلِهِمۡ يُحِبُّونَ مَنۡ هَاجَرَ إِلَيۡهِمۡ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمۡ حَاجَةٗ مِّمَّآ أُوتُواْ وَيُؤۡثِرُونَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ وَلَوۡ كَانَ بِهِمۡ خَصَاصَةٞۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفۡسِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

9..እነዚያ ከበፊታቸው ሀገሪቱን መዲና መኖሪያ ያደረጓትና እምነት በልባቸው የሰረጸባቸው ወደ እነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ:: ስደተኞችም ከተሰጡት ነገር ላይ በልቦቻቸው ውስጥ እንኳን ምንም ቅሬታን አያሳድሩም:: በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸዉም እንኳ በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ያስቀድማሉ:: ከነፍሶቻቸው ንፉግነት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ የተሳካለቸውና ምኞታቸውን አግኚዎች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير: