আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

አል ጃሲያህ

external-link copy
1 : 45

حمٓ

1. ሓ፤ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 45

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

2. የመጽሐፉ መወረድ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 45

إِنَّ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ

3. በሰማያትና በምድር ውስጥ ለአማኞች ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 45

وَفِي خَلۡقِكُمۡ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يُوقِنُونَ

4. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን በመፍጠር እና ከተንቀሳቃሽ ነገሮች በምድር ላይ የሚበተነውን ሁሉ በመፍጠሩ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 45

وَٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن رِّزۡقٖ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَا وَتَصۡرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ

5. በሌሊትና በቀን መተካካትም፤ አላህ ከሰማይ ባወረደው ሲሳይ (ዝናብ) በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው በማድረጉ፤ ንፋሶችንም (በየ አቅጣጫው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ በቂ ማስረጃዎች አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 45

تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۖ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤۡمِنُونَ

6. እነዚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የሆኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው:: ከአላህና ከማስረጃዎቹ በኋላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ? info
التفاسير:

external-link copy
7 : 45

وَيۡلٞ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ውሸታም፤ ኃጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት (ጥፋት ተገባው)። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 45

يَسۡمَعُ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٖ

8. የአላህን አናቅጽ በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ ይሰማል:: ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማ ሆኖ በክህደቱ ላይ ይዘወትራል:: እናም እርሱን በአሳማሚ ቅጣት አብስረው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 45

وَإِذَا عَلِمَ مِنۡ ءَايَٰتِنَا شَيۡـًٔا ٱتَّخَذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ

9. ከአናቅጻችንም አንዲትን ነገር ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ ያደርጋታል:: እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 45

مِّن وَرَآئِهِمۡ جَهَنَّمُۖ وَلَا يُغۡنِي عَنۡهُم مَّا كَسَبُواْ شَيۡـٔٗا وَلَا مَا ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡلِيَآءَۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ

10. ከፊታቸዉም ገሀነም አለች:: የሰበሰቡት ሀብትም ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸዉም:: ከአላህ ሌላም ረዳቶች ያደረጓቸው ሁሉ ምንንም አይጠቅሟቸዉም:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 45

هَٰذَا هُدٗىۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ لَهُمۡ عَذَابٞ مِّن رِّجۡزٍ أَلِيمٌ

11. ይህ ቁርኣን መሪ ነው:: እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ የካዱት ሁሉ ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት ድርሻቸው አለባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 45

۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَكُمُ ٱلۡبَحۡرَ لِتَجۡرِيَ ٱلۡفُلۡكُ فِيهِ بِأَمۡرِهِۦ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

12. አላህ ያ ባህርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታዉም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናንተ የገራላችሁ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 45

وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مِّنۡهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ

13. ለእናንተ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ያገራላችሁ ነው። በዚህ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት። info
التفاسير: