আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
15 : 4

وَٱلَّٰتِي يَأۡتِينَ ٱلۡفَٰحِشَةَ مِن نِّسَآئِكُمۡ فَٱسۡتَشۡهِدُواْ عَلَيۡهِنَّ أَرۡبَعَةٗ مِّنكُمۡۖ فَإِن شَهِدُواْ فَأَمۡسِكُوهُنَّ فِي ٱلۡبُيُوتِ حَتَّىٰ يَتَوَفَّىٰهُنَّ ٱلۡمَوۡتُ أَوۡ يَجۡعَلَ ٱللَّهُ لَهُنَّ سَبِيلٗا

15. እነዚያ ከሴቶቻችሁ መካከል ዝሙትን የሚሰሩ በእነርሱ ላይ ከናንተ የሆነን አራት ታማኝ ወንዶችን አስመስክሩባቸው:: ከመሰከሩባቸዉም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለእነርሱ ሌላ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውስጥ ያዟቸው(እሰሯቸው::) info
التفاسير:

external-link copy
16 : 4

وَٱلَّذَانِ يَأۡتِيَٰنِهَا مِنكُمۡ فَـَٔاذُوهُمَاۖ فَإِن تَابَا وَأَصۡلَحَا فَأَعۡرِضُواْ عَنۡهُمَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ تَوَّابٗا رَّحِيمًا

16. እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ዝሙትን የሚሰሩትን አሰቃዩዋቸው (በሚገባ ቅጧቸው):: ቢጸጸቱና ስራቸውን ቢያሳምሩ ግን እነርሱን ተዋቸው (አታሰቃዩዋቸው።) አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 4

إِنَّمَا ٱلتَّوۡبَةُ عَلَى ٱللَّهِ لِلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٖ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٖ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

17. ጸጸትን መቀበል ከአላህ በኩል ለእነዚያ ኃጢአትን በስህተት ለሚሰሩና ከዚያም ወዲያውኑ ለሚጸጸቱ ነው:: እነዚያንማ አላህ ከእነርሱ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና፣ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 4

وَلَيۡسَتِ ٱلتَّوۡبَةُ لِلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ حَتَّىٰٓ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ إِنِّي تُبۡتُ ٱلۡـَٰٔنَ وَلَا ٱلَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمۡ كُفَّارٌۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا

18. ጸጸትን መቀበል ለእነዚያ ኃጢአቶችን ለሚሰሩና ልክ ሞት በመጣባቸው ጊዜ «አሁን ተጸጸትኩ።» ለሚሉና ለእነዚያም ከሓዲያን ሆነው ለሚሞቱ አይደለም:: ለእነርሱማ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا يَحِلُّ لَكُمۡ أَن تَرِثُواْ ٱلنِّسَآءَ كَرۡهٗاۖ وَلَا تَعۡضُلُوهُنَّ لِتَذۡهَبُواْ بِبَعۡضِ مَآ ءَاتَيۡتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأۡتِينَ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِن كَرِهۡتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكۡرَهُواْ شَيۡـٔٗا وَيَجۡعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيۡرٗا كَثِيرٗا

19. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም:: በመልካም ተኗኗሯቸው:: ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ:: አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና:: info
التفاسير: