আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
48 : 39

وَبَدَا لَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

48. ለእነርሱም የሰሯቸው መጥፎዎቹ ይገልጹላቸዋል:: በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 39

فَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ضُرّٞ دَعَانَا ثُمَّ إِذَا خَوَّلۡنَٰهُ نِعۡمَةٗ مِّنَّا قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلۡمِۭۚ بَلۡ هِيَ فِتۡنَةٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

49. ሰውም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ይጠራናል:: ከዚያም ከእኛ የሆነውን ጸጋ በሰጠነው ጊዜ «እርሱን የተሰጠሁት በእውቀቴ ብቻ ነው።» ይላል:: ይልቁንም እርሷ (ጸጋይቱ) መፈተኛ ናት:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 39

قَدۡ قَالَهَا ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

50. እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ይችኑ ቃል በእርግጥ ብለዋታል:: ይሰሩት የነበሩትም ነገር ከእነርሱ አልጠቀማቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 39

فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْۚ وَٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ هَٰٓؤُلَآءِ سَيُصِيبُهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ

51. የሰሯቸዉም መጥፎዎች ቅጣት አገኛቸው:: ከእነዚህም እነዚያ የበደሉት የሰሯቸውን መጥፎዎች ፍዳ በእርግጥ ይነካቸዋል:: እነርሱም አምላጮች አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 39

أَوَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ

52. አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ፤ ለሚሻው ሰው የሚያጠብም መሆኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ህዝቦች ሁሉ አያሌ ግሳጼዎች አሉበት:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 39

۞ قُلۡ يَٰعِبَادِيَ ٱلَّذِينَ أَسۡرَفُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُواْ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና:: እነሆ እርሱ መሀሪዉና አዛኙ ነውና።» info
التفاسير:

external-link copy
54 : 39

وَأَنِيبُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّكُمۡ وَأَسۡلِمُواْ لَهُۥ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَكُمُ ٱلۡعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

54. (ሰዎች ሆይ!) ቅጣቱ ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ:: ለእርሱም ታዘዙ:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 39

وَٱتَّبِعُوٓاْ أَحۡسَنَ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَكُمُ ٱلۡعَذَابُ بَغۡتَةٗ وَأَنتُمۡ لَا تَشۡعُرُونَ

55. እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን መልካሙን መጽሐፍ ተከተሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 39

أَن تَقُولَ نَفۡسٞ يَٰحَسۡرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِي جَنۢبِ ٱللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ ٱلسَّٰخِرِينَ

56. የካደች ነፍስ ሁሉ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስሆን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ! ጸጸቴ!» የምትል እንዳትሆን info
التفاسير: