আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
64 : 27

أَمَّن يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَمَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

64. ወይስ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው፤ ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣቸሁ አምላክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? እውነተኞች እንደሆናችሁ አስረጃችሁን አምጡ በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 27

قُل لَّا يَعۡلَمُ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلۡغَيۡبَ إِلَّا ٱللَّهُۚ وَمَا يَشۡعُرُونَ أَيَّانَ يُبۡعَثُونَ

65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም:: አላህ ግን ያውቀዋል:: መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 27

بَلِ ٱدَّٰرَكَ عِلۡمُهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّنۡهَاۖ بَلۡ هُم مِّنۡهَا عَمُونَ

66. በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም ሁኔታ ማወቃቸው ተሟላን? አይደለም። እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእውነትም እነርሱ ከእርሷ እውሮች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 27

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا تُرَٰبٗا وَءَابَآؤُنَآ أَئِنَّا لَمُخۡرَجُونَ

67. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ፡- «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በሆንን ጊዜ እንደ ገና ከመቃብር የምንወጣ ነን? info
التفاسير:

external-link copy
68 : 27

لَقَدۡ وُعِدۡنَا هَٰذَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

68. «ይህንን እኛም ሆነ ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረንበታል:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
69 : 27

قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልክቱ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 27

وَلَا تَحۡزَنۡ عَلَيۡهِمۡ وَلَا تَكُن فِي ضَيۡقٖ مِّمَّا يَمۡكُرُونَ

70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም ላይ አትዘን:: ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 27

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

71. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
72 : 27

قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ رَدِفَ لَكُم بَعۡضُ ٱلَّذِي تَسۡتَعۡجِلُونَ

72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጧል።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
73 : 27

وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَشۡكُرُونَ

73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 27

وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَعۡلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمۡ وَمَا يُعۡلِنُونَ

74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 27

وَمَا مِنۡ غَآئِبَةٖ فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٍ

75. በሰማይም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም:: ገላጭ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 27

إِنَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ يَقُصُّ عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَكۡثَرَ ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

76. ይህ ቁርኣን እነዚያ የኢስራኢል ልጆች እነርሱ በእርሱ ላይ የሚለያዩበትን ጉዳይ አብዛኛውን ይነግራል:: info
التفاسير: