আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
68 : 25

وَٱلَّذِينَ لَا يَدۡعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ وَلَا يَقۡتُلُونَ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَا يَزۡنُونَۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ يَلۡقَ أَثَامٗا

68. እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንን የሚፈጽም ሰው ወንጀለኛ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 25

يُضَٰعَفۡ لَهُ ٱلۡعَذَابُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَيَخۡلُدۡ فِيهِۦ مُهَانًا

69. በትንሳኤ ቀን ቅጣት ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ዘልአለሙን ይኖራል:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 25

إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلٗا صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ يُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِهِمۡ حَسَنَٰتٖۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

70. ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 25

وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَإِنَّهُۥ يَتُوبُ إِلَى ٱللَّهِ مَتَابٗا

71. ተጸጽቶ የተመለሰና መልካምን ተግባር የሰራ እርሱ በአላህ ዘንድ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 25

وَٱلَّذِينَ لَا يَشۡهَدُونَ ٱلزُّورَ وَإِذَا مَرُّواْ بِٱللَّغۡوِ مَرُّواْ كِرَامٗا

72. እነዚያ በሐሰት የማይጣዱ፤ በውድቅ ቃል (ተናጋሪ) አጠገብም ባለፉ ጊዜ የተከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 25

وَٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ لَمۡ يَخِرُّواْ عَلَيۡهَا صُمّٗا وَعُمۡيَانٗا

73. እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ በተገሠጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች ሆነው እንጂ) ደንቆሮዎችና እውሮች ሆነው በእርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 25

وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبۡ لَنَا مِنۡ أَزۡوَٰجِنَا وَذُرِّيَّٰتِنَا قُرَّةَ أَعۡيُنٖ وَٱجۡعَلۡنَا لِلۡمُتَّقِينَ إِمَامًا

74. እነዚያ «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን።» የሚሉ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 25

أُوْلَٰٓئِكَ يُجۡزَوۡنَ ٱلۡغُرۡفَةَ بِمَا صَبَرُواْ وَيُلَقَّوۡنَ فِيهَا تَحِيَّةٗ وَسَلَٰمًا

75. እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ:: በእርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይሰጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 25

خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ حَسُنَتۡ مُسۡتَقَرّٗا وَمُقَامٗا

76. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው (ይሰጣሉ):: መርጊያና መኖሪያይቱ ገነት አማረች:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 25

قُلۡ مَا يَعۡبَؤُاْ بِكُمۡ رَبِّي لَوۡلَا دُعَآؤُكُمۡۖ فَقَدۡ كَذَّبۡتُمۡ فَسَوۡفَ يَكُونُ لِزَامَۢا

77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ) «ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር:: አስተባበላችሁ:: እናም ወደ ፊት ቅጣት ያዣችሁ ይሆናል።» በላቸው። info
التفاسير: