আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
76 : 17

وَإِن كَادُواْ لَيَسۡتَفِزُّونَكَ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ لِيُخۡرِجُوكَ مِنۡهَاۖ وَإِذٗا لَّا يَلۡبَثُونَ خِلَٰفَكَ إِلَّا قَلِيلٗا

76. ከምድሪቱ (ከዓረብ) ምድር ከእርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ:: ያን ጊዜም ካንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 17

سُنَّةَ مَن قَدۡ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ مِن رُّسُلِنَاۖ وَلَا تَجِدُ لِسُنَّتِنَا تَحۡوِيلًا

77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደ ላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ ይጠፋ ነበር፤ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም (አይለወጥም)። info
التفاسير:

external-link copy
78 : 17

أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِدُلُوكِ ٱلشَّمۡسِ إِلَىٰ غَسَقِ ٱلَّيۡلِ وَقُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِۖ إِنَّ قُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِ كَانَ مَشۡهُودٗا

78. ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ:: የጎህንም ሶላት ስገድ:: የጎህ ሶላት መላዕክት የሚገኙበት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 17

وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَتَهَجَّدۡ بِهِۦ نَافِلَةٗ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبۡعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامٗا مَّحۡمُودٗا

79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሌሊት ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በቁርኣን ስገድ:: ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃልና:: info
التفاسير:

external-link copy
80 : 17

وَقُل رَّبِّ أَدۡخِلۡنِي مُدۡخَلَ صِدۡقٖ وَأَخۡرِجۡنِي مُخۡرَجَ صِدۡقٖ وَٱجۡعَل لِّي مِن لَّدُنكَ سُلۡطَٰنٗا نَّصِيرٗا

80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በልም: «ጌታዬ ሆይ! የተወደደን መግባት አስገባኝ፤ የተወደደንም መውጣት አስወጣኝ:: ለእኔም ካንተ ዘንድ የተረዳን ስልጣን አድርግልኝ።» info
التفاسير:

external-link copy
81 : 17

وَقُلۡ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَزَهَقَ ٱلۡبَٰطِلُۚ إِنَّ ٱلۡبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقٗا

81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
82 : 17

وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلۡقُرۡءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٞ وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارٗا

82. ከቁርኣን ለአማኞች መድሓኒትና እዝነት የሆነን እናወርዳለን በዳዮችንም ኪሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 17

وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ كَانَ يَـُٔوسٗا

83. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከምስጋና ይዞራል ጎኑንም ከእውነት ያርቃል:: ችግርም በነካው ጊዜ ተስፋ ቆራጭ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 17

قُلۡ كُلّٞ يَعۡمَلُ عَلَىٰ شَاكِلَتِهِۦ فَرَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَنۡ هُوَ أَهۡدَىٰ سَبِيلٗا

84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም በሚመስለው መንገድ ላይ ይሠራል:: ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የሆነውን አዋቂ ነው።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
85 : 17

وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنۡ أَمۡرِ رَبِّي وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِ إِلَّا قَلِيلٗا

85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን ከሩህ ይጠይቁሃል። «ሩህ ከጌታዬ ነገር ነው:: ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 17

وَلَئِن شِئۡنَا لَنَذۡهَبَنَّ بِٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ ثُمَّ لَا تَجِدُ لَكَ بِهِۦ عَلَيۡنَا وَكِيلًا

86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብንሻ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን በእርግጥ እንወስድብሃለን:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ በእርሱ ለማስመለስ ተያዢን አታገኝም:: info
التفاسير: