আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
89 : 10

قَالَ قَدۡ أُجِيبَت دَّعۡوَتُكُمَا فَٱسۡتَقِيمَا وَلَا تَتَّبِعَآنِّ سَبِيلَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ

89. (አላህም) ፡- «ጸሎታችሁ ተሰምታለች:: ቀጥም በሉ:: የእነዚያን የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ።» አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 10

۞ وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتۡبَعَهُمۡ فِرۡعَوۡنُ وَجُنُودُهُۥ بَغۡيٗا وَعَدۡوًاۖ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدۡرَكَهُ ٱلۡغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِيٓ ءَامَنَتۡ بِهِۦ بَنُوٓاْ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ

90. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሳለፍናቸው:: ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው:: የመስመጥ አደጋ ባገኘውም ጊዜ «አመንኩ:: እነሆ ከዚያ የእሥራኤል ልጆች ካመኑበት አምላክ በስተቀር ሌላ የእውነት አምላክ የለም:: እኔም ከታዛዦቹ (ሙስሊሞች) አንዱ ነኝ።» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 10

ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ عَصَيۡتَ قَبۡلُ وَكُنتَ مِنَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

91. «ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክና ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን ታምናለህን?» ተባለ። info
التفاسير:

external-link copy
92 : 10

فَٱلۡيَوۡمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنۡ خَلۡفَكَ ءَايَةٗۚ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِ عَنۡ ءَايَٰتِنَا لَغَٰفِلُونَ

92. እናም ዛሬ ከኋላህ ለሚመጡ ትውልዶች ተዓምር ትሆን ዘንድ አካልህን (ከባሕሩ) እናወጣሀለን ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዐምሮቻችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 10

وَلَقَدۡ بَوَّأۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ مُبَوَّأَ صِدۡقٖ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ فَمَا ٱخۡتَلَفُواْ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

93. የኢስራኢልን ልጆችም ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው:: እውቀትም እስከመጣላቸው ድረስ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል:: info
التفاسير:

external-link copy
94 : 10

فَإِن كُنتَ فِي شَكّٖ مِّمَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ فَسۡـَٔلِ ٱلَّذِينَ يَقۡرَءُونَ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكَۚ لَقَدۡ جَآءَكَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ

94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)) ወደ አንተ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ከሆንክ እነዚያን ካንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ሰዎች ጠይቅ:: እውነቱ ከጌታህ ዘንድ መጥቶልሃል:: እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 10

وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ የአላህን አናቅጽ ካስተባበሉት ሰዎች አትሁን:: ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና:: info
التفاسير:

external-link copy
96 : 10

إِنَّ ٱلَّذِينَ حَقَّتۡ عَلَيۡهِمۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ

96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው ሰዎች አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 10

وَلَوۡ جَآءَتۡهُمۡ كُلُّ ءَايَةٍ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ

97. ተዓምራት ሁሉ ቢመጣላቸዉም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ(አያምኑም):: info
التفاسير: