আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ- মুহাম্মদ ছাদিক

পৃষ্ঠা নং:close

external-link copy
79 : 12

قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأۡخُذَ إِلَّا مَن وَجَدۡنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّظَٰلِمُونَ

«ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠብቃለን፡፡ እኛ ያን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
80 : 12

فَلَمَّا ٱسۡتَيۡـَٔسُواْ مِنۡهُ خَلَصُواْ نَجِيّٗاۖ قَالَ كَبِيرُهُمۡ أَلَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ أَبَاكُمۡ قَدۡ أَخَذَ عَلَيۡكُم مَّوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبۡلُ مَا فَرَّطتُمۡ فِي يُوسُفَۖ فَلَنۡ أَبۡرَحَ ٱلۡأَرۡضَ حَتَّىٰ يَأۡذَنَ لِيٓ أَبِيٓ أَوۡ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ لِيۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ

ከርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ፡፡ ታላቃቸው አለ «አባታቸሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ (የምስርን) ምድር አልለይም፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
81 : 12

ٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيكُمۡ فَقُولُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبۡنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدۡنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمۡنَا وَمَا كُنَّا لِلۡغَيۡبِ حَٰفِظِينَ

«ወደ አባታችሁ ተመለሱ በሉትም፡- አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ፡፡ ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፡፡ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
82 : 12

وَسۡـَٔلِ ٱلۡقَرۡيَةَ ٱلَّتِي كُنَّا فِيهَا وَٱلۡعِيرَ ٱلَّتِيٓ أَقۡبَلۡنَا فِيهَاۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

«ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
83 : 12

قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٌۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَنِي بِهِمۡ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ

(ያዕቆብ) «አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ (ሠራችሁትም)፡፡ መልካምም ትእግስት (ማድረግ) አለብኝ፡፡ እነርሱን (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፡፡ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
84 : 12

وَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبۡيَضَّتۡ عَيۡنَاهُ مِنَ ٱلۡحُزۡنِ فَهُوَ كَظِيمٞ

ከእነሱም ዘወር አለና «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
85 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ تَفۡتَؤُاْ تَذۡكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوۡ تَكُونَ مِنَ ٱلۡهَٰلِكِينَ

(እነርሱም) «በአላህ እንምላለን፡፡ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
86 : 12

قَالَ إِنَّمَآ أَشۡكُواْ بَثِّي وَحُزۡنِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡ info
التفاسير: