ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
15 : 29

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَصۡحَٰبَ ٱلسَّفِينَةِ وَجَعَلۡنَٰهَآ ءَايَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ

ኑሕንና የመርከቢቱንም ጓዶች አዳናቸው፡፡ እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 29

وَإِبۡرَٰهِيمَ إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُۖ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «አላህን ተገዙ ፍሩትም፡፡ ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 29

إِنَّمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡثَٰنٗا وَتَخۡلُقُونَ إِفۡكًاۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمۡلِكُونَ لَكُمۡ رِزۡقٗا فَٱبۡتَغُواْ عِندَ ٱللَّهِ ٱلرِّزۡقَ وَٱعۡبُدُوهُ وَٱشۡكُرُواْ لَهُۥٓۖ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

«ከአላህ ሌላ የምትገዝዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፡፡ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፡፡ ተገዙትም፡፡ ለእርሱም አመሰግኑ፡፡ ወደእርሱ ትመለሳላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 29

وَإِن تُكَذِّبُواْ فَقَدۡ كَذَّبَ أُمَمٞ مِّن قَبۡلِكُمۡۖ وَمَا عَلَى ٱلرَّسُولِ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ

«ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል፡፡ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
19 : 29

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ كَيۡفَ يُبۡدِئُ ٱللَّهُ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥٓۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ

አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀመር ከዚያም እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን? ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 29

قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ بَدَأَ ٱلۡخَلۡقَۚ ثُمَّ ٱللَّهُ يُنشِئُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأٓخِرَةَۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

«በምድር ላይ ኺዱ፤ መፍጠርንም እንዴት እንደ ጀመረ ተመልከቱ፡፡ ከዚያም፤ አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 29

يُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَيَرۡحَمُ مَن يَشَآءُۖ وَإِلَيۡهِ تُقۡلَبُونَ

የሚሻውን ሰው ይቀጣል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 29

وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ

እናንተም በምድርም ኾነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳትም ተከላካይም ምንም የላችሁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 29

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَلِقَآئِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ يَئِسُواْ مِن رَّحۡمَتِي وَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

እነዚያም በአላህ አንቀጾችና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ፡፡ እነዚያም ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ info
التفاسير: